#FastMereja I የአለም አቀፉ የቁንጅና ውድድር (Miss World) አሸናፊዎችን የሚለይበትንና ተወዳዳሪዎች የሚመዘኑባቸው ከውጭ አካላዊ ውበት ይልቅ ለተወዳዳሪዎች የበጎ አድራጎት ስራዎች፣ የንግግር ችሎታ፣ አካላዊ ብቃትና ልዩ ክህሎቶች ከፍተኛ ነጥብ የሚሰጥበት ነው።
ተወዳዳሪዎች ወደ መጨረሻው የዘውድ ምዕራፍ ለማለፍ “Fast Track” በተሰኙ መስፈርቶች አልፈው በዳኞች ይገመገማሉ።
ዓለም አቀፉ የሚስ ወርልድ ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ተወዳዳሪዎችን ለተፈለገው ዘውድ የሚያበቁትና ዳኞች ነጥብ የሚሰጡባቸው ዋና ዋና የምዘና መስፈርቶች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፦
📌 Beauty with a Purpose
ይህ መስፈርት የውድድሩ ዋናና ትልቁ ማዕከል እንደሆነ ተገልጻል። ተወዳዳሪዎች በሀገራቸው ውስጥ የሚመሩትን ወይም የፈጠሩትን የበጎ አድራጎትና የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክት ለዳኞች ያቀርባሉ። የማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረትና ያመጡት ለውጥ ከፍተኛውን ነጥብ ያስገኛል።
📌 Head-to-Head Challenge
የተወዳዳሪዎችን በህዝብ ፊት የመናገር ብቃት፣ የማህበራዊ ግንኙነት ችሎታ፣ አጠቃላይ እውቀትና የአስተሳሰብ የበሰለነት ደረጃ የሚመዘንበት ምዕራፍ ነው።
📌 የክህሎትና ፈጠራ ውድድር (Talent Round)
ተወዳዳሪዎች እንደ ዘፈን፣ ውዝዋዜ፣ ሙዚቃ መሣሪያ መጫወት ወይም ሌሎች ልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ ፈጠራዎቻቸውን በመድረክ ላይ በማቅረብ ችሎታቸውን ያሳያሉ።
📌 የፋሽንና ሞዴሊንግ ብቃት (Top Model)
ተወዳዳሪዎች ያላቸውን የመድረክ ላይ መተማመን፣ የፋሽን አቀራረብ፣ የአካሄድ ስልትና የልብስ አሰራርን የማስተዋወቅ ብቃት በዳኞች የሚገመገምበት መስፈርት ነው።
📌 የስፖርትና አካል ብቃት (Sports Challenge)
ተወዳዳሪዎች ያላቸውን አካላዊ ጥንካሬ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴና የአካል ብቃት የሚያሳዩበት ልዩ የውድድር ክፍል ነው።
📌 የማህበራዊ ሚዲያና መልቲሚዲያ (Multimedia)
ተወዳዳሪዎች በዲጂታል አማራጮች ከህዝብ ጋር ያላቸውን ቁርኝት፣ የሚያዘጋጁትን የመረጃ ይዘትና የሚያገኙትን የህዝብ ድጋፍ መጠን ለመለካት የሚያገለግል መስፈርት እንደሆነ ተመልክቷል። ይህ መስፈርት አሁን ህዝቡ ድምጽ እየሰጠበት ያለው ውስጥ ይካተታል።
Source: FastMereja









No comments yet.