የክብር ዶክተር አርቲስት ማህሙድ አህመድ “ለታሪክ” የተሰኘ የመጨረሻ አልበሙን ሊለቅ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ለስድስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የማይተካ አስተዋጽኦ ያበረከተው የክብር ዶክተር አርቲስት ማህሙድ አህመድ “ለታሪክ” የተሰኘውን 26ኛ እና የመጨረሻ አልበሙን ለአድማጮች ሊያደርስ መሆኑን ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አበሰረ።

​ይህ አልበም የቀደሙትን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቅርሶች፣ ለዛና ወግ ሳይለቁ ለአዲሱ ትውልድ ለማስረከብ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የአርቲስቱን ልዩ የመድረክና የድምፅ ስልት መሠረት ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል። በስራው ላይ ዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች እና ባህላዊ የቅኝት ድምፆች በተዋጣለት መልኩ የተዋሃዱበት ሲሆን፣ የፍቅር፣ የሀገር፣ የህይወት ፍልስፍና እና ማህበራዊ እሴቶችን የሚያንፀባርቁ አዳዲስና በትዝታ የተቃኙ ስራዎች ተካተውበታል።

​በአልበሙ ዝግጅት ላይ አንጋፋ እና ወጣት የዜማና ግጥም ደራሲያን እንዲሁም የሙዚቃ አቀናባሪዎች በጋራ የተሳተፉ ሲሆን፣ አርቲስቱ ይህ አልበም የኪነ-ጥበብ ህይወቱ የመጨረሻ ስራ መሆኑን በመግለፅ አዲሱ የሙዚቃ ትውልድ የሀገርን ባህል፣ ቅኝት እና ማንነት ሳይለቅ ዘመናዊነትን እንዲቀላቅል ጥሪ አቅርቧል።

​አልበሙን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማሰራጨቱንና የማስተዋወቁን ስራ ይሳቃል ኢንተርቴይመንት ከሌሎች የሙዚቃ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር የሚያከናውነው ሲሆን፣ በSpotify, Apple Music እና YouTube ጨምሮ በሁሉም ዲጂታል መድረኮች ለህዝብ ይደርሳል። በእንቁጣጣሽ ዋዜማ አንድ ነጠላ ዜማ የሚለቀቅ ሲሆን ሙሉ አልበሙ ደግሞ በመስከረም አጋማሽ ለአድማጮች ክፍት ይደረጋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: