#Ethiopia | በቀደሙት ዘመናት ትልቅ ስጋትንና ድንጋጤን ይፈጥር የነበረው፣ በዘመናዊው የሳይንስ እውቀት ደግሞ ውብ የጠፈር ክስተት ተብሎ የሚገለጸው የጨረቃ ግርዶሽ በዛሬው ዕለት ሌሊት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ይታያል።
በዛሬው የሐሙስ አደራሽ ሌሊት በሚከሰተው በዚህ አጋጣሚ፣ ሙሉ ጨረቃ በመሬት ጥላ ስር በመሸፈኗ እስከ 96 በመቶ የሚሆነው አካሏ በመጋረድ ወደ ጥልቅ ቀይ ቀለም ሲቀየር ለመመልከት ይቻላል።
ይህ ክስተት ከአጋጣሚ ባሻገር ከአስራ አራት ቀናት በፊት በስፔን ከተስተዋለው ታላቅ የፀሐይ ግርዶሽ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለው የጠፈር ክስተት ነው።
የጨረቃ የመዞሪያ ምህዋር በ5 ዲግሪ ያህል ዘመም ያለ በመሆኑ በየወሩ ግርዶሽ ባይከሰትም፣ በዓመት ሁለት ጊዜ ግን ፀሐይ፣ መሬት እና ጨረቃ በአንድ መስመር ላይ ይሰለፋሉ።
በሥነ ፈለክ ሳይንስ የግርዶሽ ወቅት ተብሎ በሚጠራው በዚህ ጊዜ የፀሐይ እና የጨረቃ ግርዶሾች በሁለት ሳምንታት ልዩነት ውስጥ ተከታትለው መከሰታቸው ተፈጥሯዊ ሂደት ነው።
በዛሬው ሌሊት ጨረቃ በመሬት ጥላ ውስጥ ስታልፍ ሙሉ በሙሉ አትሰወርም።
ይልቁንም የመሬት ከባቢ አየር አጫጭር የሆኑትን ሰማያዊ የብርሃን ሞገዶች አስቀርቶ ረዣዥሞቹን ቀይ የብርሃን ሞገዶች ብቻ ወደ ጨረቃ ገጽታ ስለሚልካቸው፣ ጨረቃ የደም ቀለም የሚመስል ውብ እይታን ትላበሳለች።
በኢትዮጵያ የሚገኙ ተመልካቾች ይህንን ክስተት ከሌሊቱ 11 ሰዓት ከ33 ደቂቃ እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ በምዕራብ አድማስ በኩል በግልጽ ማየት ይችላሉ።
ሁነቱን ለመታዘብ ምንም ዓይነት የዓይን መከላከያ መነጽር እንደማያስፈልግና በቃላት ብቻ ቀና ብሎ መመልከት እንደሚቻል የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አስታውቋል።
ይህ አጋጣሚ የዘንድሮው ዓመት የመጨረሻው ግርዶሽ በመሆኑና ቀጣዩ መሰል ታላቅ የጨረቃ ግርዶሽ እስከ ታኅሣሥ 2021 ዓ.ም ድረስ ስለማይከሰት፣ በዛሬው ሌሊት ሰማዩ ክፍት ከሆነ ይህንን የተፈጥሮ ድንቅ ክስተት እንዲታዘቡ ተመክሯል።
#LunarEclipse #BloodMoon #Astronomy #SpaceScience #የጨረቃግርዶሽ #የተፈጥሮድንቅ #ሳይንስ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen








No comments yet.