“ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ የሀገር ሀብት ናት-ቴዎድሮስ እንዳለው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia |የአዊ ብሄ/አስ ምክር ቤትና የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር
በሀገሪቱ ከሴቶች አንደኛውን ከፍተኛ ውጤት 583/600 ላስመዘገበችው ህዳሴ ዘመኑ እውቅናና የማበረታቻ ሽልማት አበረከቱ።

ለተማሪ ህዳሴ ዘመኑ የአዊ ብሄ/አስ ምክር ቤት የላፕቶፕ ሽልማት በመስጠት እውቅና ሰጧል።

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር 190ሽህ ብር ወጪ የተደረገበት አልትራ S26 ስማርት ፎን ፣ለወላጆቿና እና ለአቶ አዲሱ የባህል አልባሳት ለአገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ100 ሽህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አበርክቷል።

በመርሃ ግብሩ የአዊ ብሄ/አስ ዋና አስተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው ፥ የማህበረሰቡ ድምር ውጤት የሆነችው ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ የሴቶችን የማድረግ አቅም በተግባር አሳይታናለች ብለዋል።ያስመዘገበችው ከፍተኛ ውጤት የትጋት፣ የጽናትና የስኬት ትልቅ ምስክር እንደሆነ ነው የተናገሩት።

የውጤታማነትና የፅናት ማሳያዋ ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ
ያስመዘገበችው ከፍተኛ ውጤት ሀገርንና አካባቢያችንን በማስተዋወቅ ” አኩርታናለች” ብለዋል።

ህዳሴ የሀገር ሀብት ናት ያሉት አስተዳዳሪው “የመጣሽበትን መንገድ በማስፋት ለሀገርና ለአለም እንድትተርፊ ውጤታማነትሽ መቀጠልና መፅናት አለበት ሲሉም መክረዋታል ።

ከህዳሴ ስኬት ጀርባ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉትን ወላጆቿን እና ትምህርት ቤቷን አቶ ቴዎድሮስ አመስግነዋል ።
ቀጣይ ለተማሪ ሄዳሴ ዘመኑ ብሄረሰብ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላት ዋና አሰተዳዳሪው ገልፀዋል።

የአዊ ብሄ/አሰ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ ደስታው አለሙ፥
የሀገር ሀብት የብሄረሰብ አስተዳደሩ ኩራት ተማሪ ዘመኑ
በችግር አለመገበር እና የረጅም ጊዜ የትጋት ውጤት ምሳሌ መሆኗን ተናግረዋል ።

የቀጣይ በርካታ ህዳሴዎችን ለማፍራት መነቃቃት እንደፈጠረችም ገልፀዋል።

ለበርካታ ተማሪዎች” የእንችላን ስንቅ ተምሳሌት” መሆኗን የገለፁት ሀላፊው ለውጤታማነቷ ድጋፍ ያደረጉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን አመስግነዋል።




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: