ቴምር ፕሮፐርቲስ በመገናኛ ለሚያስገነባው ህንፃ ከሁለት የቻይና ኩባንያዎች ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:- ቴምር ፕሮፐርቲስ በሪል እስቴት ልማት ዘርፍ ያስመዘገበውን የ10 ዓመታት ስኬታማ ጉዞ ምክንያት በማድረግ፣ ለአካባቢ ጥበቃ አርአያ ለሆኑ ወገኖች በዛሬዉ እለት በመገናኛ ወደ ጫካ ፕሮጀክት በሚወስደው እዲሱ የቴምር ፕሮፐርቲ ሳይት ዕውቅናና ስጦታ ያበረከተ ሲሆን ከሁለት የቻይና ኩባንያዎች ጋርም የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ የደን ሀብት፣ ብዝሃ ሕይወትና የሥነ-ምህዳር ሚዛንን ለመጠበቅ በየዕለቱ ከፍተኛ ሀላፊነት ተግባራትን ለሚያከናውኑ የጉለሌ እፅዋት ማዕከል 75 የደን ጠባቂ ሬንጀሮች ዕውቅናና ለሥራቸው ተስማሚ የሆነ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

በተጨማሪም “Plogging Ethiopia” የተባለውን ተቋም በመመስረት ላለፉት 6 ዓመታት በበጎ ፈቃደኝነት የወዳደቁ ፕላስቲኮችንና ቆሻሻዎችን በመሰብሰብ ለአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ለአቶ ፍሬው ከፍያለው ልዩ ዕውቅናና ስጦታ ተሰጥቷል።

የቴምር ፕሮፐርቲስ የኢቨንትና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ኡስማን መሀመድ በበኩላቸው፤ ይህ ዕውቅና ድርጅቱ የንግድ ሥራ ስኬትን ከአካባቢ ጥበቃና ከማኅበራዊ ኃላፊነት ጋር አስተስስሮ ለመሄድ ያለውን ጽኑ አቋም የሚያንጸባርቅ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ድርጅቱ በመገናኛ ጫካ አካባቢ ለሚያካሂደው ከመሬት በታች 8 ወለል (ቤዝመንት) እና ከመሬት በላይ 18 ወለል ያለው ህንፃ ግንባታ የጥራትና የደህንነት ደረጃዎችን ለማስጠበቅ ከሁለት የቻይና ኩባንያዎች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን ስምምነት ተፈራርሟል።

በተደረሰው ስምምነት መሠረት፡-Hui Chen: የመሬት ቁፋሮ (Excavation) ሥራዎችን የሚያከናዉን ሲሆን Sansheng ደግሞ የኮንክሪት አቅርቦት ኃላፊነቱን በመውሰድ በፕሮጀክቱ እንደሚሳተፉ ነዉ የተገለፀዉ።

ቴምር ፕሮፐርቲስ የደንበኞችን ፍላጎትና ምርጫ መሠረት ያደረገ የሪል እስቴት አገልግሎት በመስጠት የሚታወቅ ሲሆን፣ ወደፊትም የግንባታ ዘርፉን ከአካባቢ ጥበቃ ጋርበማስተሳሰር ለዘላቂ ልማት እንደሚሠራ አስታውቋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: