ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶችን ከታላቅ እስከ ውድቅ በማለት የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ ማድረጋቸው ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

በዚህ አወዛጋቢ ዘገባ ላይ ትራምፕ እራሳቸውን በምርጡ ደረጃ “ታላቅ” (The Greatest) በማድረግ በአንደኝነት ያስቀመጡ ሲሆን፣ የቀድሞ ተፎካካሪዎቻቸውን እና ታሪካዊ መሪዎችን በተለያዩ የደረጃ ክፍሎች መድበዋቸዋል።

​በሰንጠረዡ መሰረት ጆ ባይደን፣ ባራክ ኦባማ፣ ጂሚ ካርተር፣ ኡሊሰስ ግራንት እና ዎረን ሃርዲንግ በ”ውድቅ” (Failure) ደረጃ ውስጥ የተመደቡ ሲሆን፤ በአንጻሩ አብርሃም ሊንከን፣ ጆርጅ ዋሺንግተን፣ ፍራንክሊን ሩዝቬልት፣ ዉድሮው ቪልሰን፣ ቶማስ ጄፈርሰን እና አንዲሩ ጃክሰን በ”ታላቅ” መደብ ውስጥ ተካተዋል።

በተጨማሪም ቴዎዶር ሩዝቬልት እና ጆን አዳምስን የመሰሉ መሪዎች “ወደ ታላቅነት የተጠጉ” በሚል ሲመደቡ፣ ቢል ክሊንተንን ጨምሮ በርካታ መሪዎች በ”መካከለኛ” ደረጃ፣ እንዲሁም ጄምስ ቡካናን እና ካልቪን ኩሊጅ ደግሞ በ”ከመካከለኛ በታች” ደረጃ ላይ ተመድበዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: