በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ለቢፍቱ ባስ 20 የሀገር አቋራጭ አውቶብሶችን አስረከበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በላይነህ ክንዴ ግሩፕ በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካው ያዘጋጃቸውን 20 የሀገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ለቢፍቱ ቢዝነስ ግሩፕ አስረክቧል።

በስነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የመገጣጠሚያ ፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ አህመድ እንደገለጹት፤ ተቋማቸው አጭር ጊዜን ያስቆጠረ ቢሆንም በሀገሪቱ የሚታየውን የሕዝብ ትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ፋብሪካው ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ1 ሺህ በላይ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ገጣጥሞ ለደንበኞቹ ማስረከቡንም አክለው ገልጸዋል።

የቢፍቱ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤት አቶ ዮሐንስ ደማ በበኩላቸው፤ በላይነህ ክንዴ ግሩፕ አውቶብሶቹን በአጭር ጊዜ እና በጥራት ገጣጥሞ ማስረከቡን በመጥቀስ ምስጋና አቅርበዋል።

በተለይም የድርጅቱ ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ ደረጃቸውን የጠበቁ አውቶብሶች በሀገር ውስጥ እንዲገጣጠሙ የሚያደርጉት ጥረትና የሚያበረክቱት ሀገራዊ አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የደብረ ብርሃን ተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ከቢፍቱ በተጨማሪ ለአዋሽ፣ ድሪም፣ ሀበሻ፣ ኢትዮ ባስ፣ ፈለገ ግዮን እና ጎልደን ባስ አውቶብሶችን ገጣጥሞ ማስረከቡ ይታወቃል።

#bkg #biftubus #ethiopiatransport #debreberhan #automotive
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: