#Ethiopia | በህንዷ ሜሩቷ በተባለችው ከተማ ነዋሪዎች የከተማቸውን ገፅታ ያበላሸው የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ እንዲጸዳላቸው ለከተማው ማዘጋጃ ቤት ተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርቡም ሰሚ ማግኘት አልቻሉም ነበር።
አንዲት የከተማዋ ነዋሪ ሴት ግን ህዝቡ ያቀረበውን ጥያቄ መልስ ባለማግኘቱ ባልተለመደ መንገድ መፍትሔ ለመፈለግ አንድ ዘዴ ዘየደች።
ለፖሊስና ለአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ደውላ
“አንድ ህጻን ልጅ በተደፈነው የፍሳሽ ማስወገጃ ውስጥ ገብቷል” ፈጥናችሁ ድረሱ የሚል ጥሪ አቀረበች።
ጥሪውን ተከትሎ የከተማዋ ፖሊስ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችና የማዘጋጃ ቤት የጽዳት ሠራተኞች በከባድ ማሽነሪዎች ታጅበው ወደ ስፍራው በመጣደፍ ለ3 ሰዓታት ያህል የዘለቀ ሰፊ የመታደግ ዘመቻ አካሄዱ።
ሠራተኞቹ የጠፋውን ህፃን ፍለጋ ፍሳሹን በጥልቀት ሲቆፍሩና ሲያጸዱ የቆዩ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ምንም ዓይነት የጠፋ ህፃን አለመኖሩና ጥሪው ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑ ተረጋገጠ።
ሰራተኞቹም ወደ መጡበት ተመለሱ።
ለወራት መልስ ያልተሰጠው የህዝብ አቤቱታና ቅሬታ ያላነቃነቀውን የመንግሥት አካል አንዲት የሐሰት የአደጋ ጥሪ በሰዓታት ውስጥ ቱቦውን እንዲፀዳ አድርጋዋለች።
ጉዳዩን የተከታተሉ የአካባቢው ነዋሪዎች መደበኛ አሰራር ባልሰራበት ቦታ ፍጹም መፍትሔ ያመጣ ብልሃት ነው ብለው አድንቀውታል።
በተጨማሪም በከተማው የተከሰተው ድርጊት በአካባቢው ነዋሪዎችና በከተማው ባለስልጣናት መካከል ያለውን የመልካም አስተዳደር ክፍተት በግልጽ ያሳየ ክስተት ሆኖ አልፏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#India #Meerut #community #fakeinformation #criticises
#Sanitation #drainage
#Authorities #bureaucracy
Source: GetuTemesgen









No comments yet.