አምባሳደር ፈይሰል አሊይ በዶሃ ደማቅ የሽኝት እና የእውቅና መርሃ ግብር ተደረገላቸው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በቀጠር፣ በኢራን እና በየመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እና ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ፈይሰል አሊይ አብራሂም የስራ ጊዜያቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ደማቅ የክብር አሸኛኘት ተከናወነላቸው።

በዶሃ ሂልተን ሆቴል በተካሄደው የሽኝት ፕሮግራም ላይ አምባሳደሩ በዲፕሎማሲ አገልግሎት ዘመናቸው ለሀገርና ለዜጎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ የላቀ እውቅና እና ምስጋና ተሰጥቷቸዋል።

ይህ የእውቅና ሽልማት በዶሃና በአካባቢዋ በሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት በራስ ተነሳሽነትና በፍቅር የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል።

አምባሳደር ፈይሰል በተደረገላቸው አቀባበል እና ስጦታ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ከህዝብ የሚሰጥ እውቅና እና ሽልማት ትልቅ የሞራል ስንቅ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጠር የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ማህበር ሊቀ መንበር አቶ አሚኑ ኑሩ፣ አምባሳደሩ የሁለቱን ሀገራት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማሳደግ ካደረጉት ጥረት ባሻገር፣ ከዜጎች ጎን በመቆም ያሳዩትን ህዝብ ተኮር መሪነት አድንቀዋል።

አምባሳደሩ የታመሙትን በመጠየቅ እና የችግር ጊዜ ደጋፊ በመሆን ዲፕሎማሲ የሰዎች አገልግሎት መሆኑን በተግባር ማሳየታቸውንም ገልጸዋል።

የማህበረሰቡ አባላት በበኩላቸው አምባሳደሩ በአራት ዓመታት ቆይታቸው የዜጎችን መብት በማስጠበቅ፣ የኮምዩኒቲ ትምህርት ቤትን በማጠናከር እና የጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ እንዲሳካ ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ የኃይማኖት አባቶች እና የሴቶች ማህበራት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በየመን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላትም በበይነ መረብ ተካፍለው አምባሳደሩ ለአካባቢው ዜጎች ላደረጉት ድጋፍ ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል።

#EthiopianDiplomats #FaiselAlii #EthiopiaQatarRelations #DohaEthiopians #EthiopianDiaspora #EthiopianCommunity #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2