የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ ጥሪ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ለ2026/27 ትምህርት ዘመን በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በዲግሪ ፕሮግራሞች ለመማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የመጨረሻውን የማመልከቻ ጥሪ አስተላልፏል።

ዩኒቨርሲቲው ለቀረበው የትምህርት እድል ፍላጎቱ ያላቸው አመልካቾች እድሉ ሳያመልጣቸው አሁኑኑ ማመልከት እንደሚችሉ የገለጸ ሲሆን አመልካቾች በሚመዘገቡበት ወቅት ስልካቸውንና ኢሜይላቸውን በጥንቃቄ እንዲሞሉና ለቀጣይ መረጃዎች የኢሜይልና የስልክ መልእክቶቻቸውን እንዲከታተሉ አሳስቧል።

​እንደ መርሃ ግብሩ ገለጻ፣ለአለም አቀፍ አመልካቾች የማመልከቻው መዝጊያ መስከረም 6 ቀን 2026 ሲሆን የፈተና ጊዜያቸው ደግሞ መስከረም 8 እና 9 ቀን 2026 እንዲሆን ተወስኗል።

ለኢትዮጵያውያን አመልካቾች ደግሞ ማመልከቻው መስከረም 12 ቀን 2026 የሚዘጋ ሲሆን የመግቢያ ፈተናው መስከረም 15 ቀን 2026 ይሰጣል።

የሁለቱም ዘርፍ ተማሪዎች ትምህርት በጥቅምት 5 ቀን 2026 በይፋ የሚጀምር ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች በዩኒቨርሲቲው ድህረ ገጽ

(https://eau.edu.et) ማመልከት ወይም በስልክ ቁጥር

+251-115174600/8598

እንዲሁም በኢሜይል
etauinfo@ethiopianairlines.com ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

ማስታወሻ :- ቀን እና ዓመቱ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር የተሰላ ነው

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2