የዘምዘም ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መሊካ በድሪ የ2026 WOMANi አዋርድ የክብር ሽልማትን ተጎናጸፉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I የዘምዘም ባንክ አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መሊካ በድሪ በወለድ-ነፃ የባንክ አገልግሎት እና በፋይናንስ አካታችነት ላይ ባበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ በዓለም አቀፍ ደረጃ የ2026 WOMANi አዋርድ የክብር ሽልማት አሸናፊ በመሆን ታሪክ ሰሩ።

በማሌዢያ ኩዋላ ላምፑር በካምብሪጅ አይኤፍኤ (Cambridge IFA) አዘጋጅነት በተካሄደው የሽልማትና የእውቅና ሥነ-ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች በተገኙበት፣ ወ/ሮ መሊካ በኢስላሚክ ፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ የዓለም ሴቶች መካከል አንዷ በመሆን መመረጣቸው ተረጋግጧል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት ምክትል ሚኒስትር ሴናተር ፑዋን ማርሃማህ ሮስሊ እና የካምብሪጅ ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢስላሚክ ፋይናንስ ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ፕሮፌሰር ሁማዩን ዳርን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ መሪዎች ተገኝተዋል።

ይህ ዓለም አቀፍ እውቅና የሥራ አስፈጻሚዋ ለአሥርት ዓመታት ያሳዩትን የማይናወጥ ጽናት፣ የረጅም ዓመታት የሙያ ተሞክሮ እና ግልጽ ዓላማ ያለው የአመራር ብቃት የሚያስመሰክር ከመሆኑም በላይ ለዘምዘም ባንክና ለሀገራችን ኢትዮጵያ ታላቅ የኩራት ምንጭ ሆኗል። ወ/ሮ መሊካ በድሪ ለተቀዳጁት ለዚህ ታሪካዊ ስኬትና በዓለም አቀፍ መድረክ ሀገራቸውን በክብር ላስጠሩበት ድል፣ ለባንኩ ቤተሰቦችና ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈናል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1