#Ethiopia | ታዋቂዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ፕሮፌሰር ሠናይት ፍስሐ በአህጉሪቱ የጤና ዘርፍ ላበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋጽኦ እና ላደረጉት የማያቋርጥ ድጋፍ እውቅና ለመስጠት በአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከያ ማዕከል ግቢ ውስጥ የሐውልት ምስላቸው ተሰርቶ ይፋ ሆኗል።
የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጂን ካሴያ በተገኙበት በተካሄደው የሥነ ሥርዓት መርሃ ግብር ላይ ፕሮፌሰር ሠናይት የአፍሪካ የጤና ተቋማትን ለማጠናከር፣ አጋርነትን ለማስፋፋት እና የአህጉሪቱን የጤና አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ላሳዩት የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነትና የላቀ አመራር ይህ እውቅና እንደተሰጣቸው ተገልጿል።
ማዕከሉ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ፕሮፌሰር ሠናይት ፍስሐ በሙያተኞችና በተቋማት ግንባታ ላይ በሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች አማካኝነት አፍሪካ የራሷን የጤና የወደፊት እድል በራሷ የመቅረጽ አቅም እንዳላት በተግባር ያስመሰከሩ መሪያችን ናቸው ብሏል።
#ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen









No comments yet.