#Ethiopia | ዶናልድ ትራምፕ የ9/11 ጥቃት 25ኛ ዓመት መታሰቢያን በኒዮርክ ከመገኘት ይልቅ በፔንታገን ንግግር በማድረግ ሊያከብሩ ነው።
በፔንታገን የተለየ መድረክ ማዘጋጀታቸውም ታውቋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመስከረም 11 የሽብር ጥቃት 25ኛ ዓመት መታሰቢያን በኒውዮርክ በሚገኘው “ግራውንድ ዜሮ” ከመገኘት ይልቅ በፔንታጎን እንደሚገኙ ተገለፀ።
ፕሬዝዳንቱ ቀኑን በፔንታጎን በሚያደርጉት ንግግር ለማሰብ ማቀዳቸውን ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ጠቅሶ ሲኤንኤን ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ በዓመቱ መታሰቢያ ላይ ንግግር ለማድረግ ይፈልጋሉ ነገር ግን በኒውዮርክ ግራውንድ ዜሮ በሚካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ፖለቲከኞች ንግግር እንዳያደርጉ እገዳ ተጥሏል።
ከ2012 ጀምሮ በኒውዮርኩ መታሰቢያ ቦታ ላይ የሚካሄደው ሥነ ሥርዓት ከፖለቲካ ነፃ እንዲሆን እና ትኩረቱ የጉዳቱ ሰለባ በሆኑ ቤተሰቦች ላይ ብቻ እንዲሆን በመደረጉ ፖለቲከኞች ታዳሚ እንጂ መድረክ ላይ ወጥተው ንግግር እንዲያደርጉ አይፈቀድላቸውም።
ትራምፕ መታሰቢያውን በፔንታገን በሚያደርጉት ንግግር ሲያከብሩ ምክትል ፕሬዝዳንታቸው ጄዲ ቫንስ አስተዳደራቸውን ወክለው በኒውዮርክ በሚካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።
በኒዮርክ የተወለዱት ትራምፕ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ የ9/11 መታሰቢያዎች ላይ በታዳሚነት ሲሳተፉ ነበር።
ዘንድሮ ግን ፕሬዝዳንቱ ንግግራቸውን ለማቅረብ የወሰኑት በፔንታጎን መሆኑን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#America #NewYork
#DonaldTrump #president
#JdVance #attack #groundzero
Source: GetuTemesgen









No comments yet.