#Ethiopia | የሀኪሞች ”አብቅቷል” የሚለው ቃል በሸርሊ ህይወት ላይ ታላቅ ድንጋጤን ፈጥሮ ነበር። ህመሙ ወደ ጡቷ፣ አጥንቶቿና የሰውነት ክፍሎቿ በመስፋፋቱ በአራተኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ሊታከም እንደማይችል የገለጹላት ሀኪሞቿ በምድር ላይ ለመኖር ያላትን እድል የ90 ቀናት ገደብ ብቻ ሰጧት።
ህመሙ እየበረታና መራመድ እንኳ እየከበዳት በመጣበት በዚያ አስጨናቂ ወቅት በፍርሃት ለመዋጥ ብትቃረብም እሷና ባለቤቷ ማርክ ግን ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ በእምነታቸው ለመጽናት ወሰኑ። ባለቤቷ ማርክ በየቀኑ በጸሎትና በመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት በመደገፍ ለባለቤቱ ፈውስ ይጸልይ ነበር።
በሂደቱም ከተሰጣት ከባድ የላብ አወጣጥና የሰውነት ማፅዳት ህክምና፣ እንቅስቃሴ እና ጥብቅ የአመጋገብ ስርዓት ጎን ለጎን ወዳጅ ዘመዶቿ እና የቤተክርስቲያን አባላት በጾምና በጸሎት ይደግፏት ነበር።
ከህመሟ ምርመራ ሶስት ሳምንታት በኋላ ከተመለከተችው ህልም እና ከፈጣሪዋ ከተቀበለችው የተስፋ ቃል በመነሳት ውስጣዊ ብርታትን ያገኘችው ሸርሊ ከቀን ወደ ቀን ጥንካሬዋ እየተመለሰ መጣ።
የ90 ቀናት ገደቧ ተጠናቆ ለምርመራ ወደ ሀኪሞች ዘንድ ስትመለስ ግን የህክምና ባለሙያዎቹን በከፍተኛ ሁኔታ ያስደነቀ ተአምር ተከሰተ።
የተደረገላት የስካን ምርመራ በሰውነቷ ውስጥ ምንም አይነት የካንሰር ህዋስ አለመኖሩንና ሙሉ በሙሉ ከበሽታው ነፃ መሆኗን አበሰራት። የህክምና ባለሙያዋም “አራተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ካንሰር ሙሉ በሙሉ ሲጠፋ ይህ በእርግጥም ተአምር ነው” ሲሉ ተደመጡ።
ይኸው ክስተት ከተፈጸመ ከአስር ዓመታት በላይ ያለፉ ቢሆንም፣ ሸርሊ ዛሬም ድረስ ሙሉ በሙሉ ከካንሰር ነፃ ሆና በደስታና በጤና በመኖር ላይ ትገኛለች።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.