ከጳጉሜን 2 ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል
#Ethiopia | ከጳጉሜን መጨረሻ እስከ መስቀል በዓል ማጠናቀቂያ ድረስ የሚዘልቀው የኮንታ ብሔር የዘመን መለወጫ ህንግጫ በልምላሜና በተስፋ ታጅቦ ሊከበር ዝግጅት ተጠናቋል።
በኮንታዎች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ይህ ባህላዊ በዓል፣ አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት በፍስሐ እና በደስታ የሚቀበሉበት የማንነት መገለጫ ነው።
የህንግጫ ትርጉም ያማረ፣ ያጌጠ እና የለመለመ ማለት ሲሆን፣ መስከረም ሲጠባና አደይ አበባ ምድሩን ሲሸፍነው የኮንታ ቀዬዎች ልዩ ውበት ይለብሳሉ።
በበዓሉ ወቅት ህብረተሰቡ አብሮነቱንና ፍቅሩን የሚያጠናክርበት፣ ወዳጅ ዘመድ የሚጠያየቅበት፣ እንደሁም ያለው ለሌለው አካፍሎ የሚመገብበት የወል መድረክ ይፈጠራል።
እንደ ባህሉ ሥርዓት ከቤት እስከ ደጃፍ ጽዳት ይከናወናል፤ የአዲሱ ዓመት ማብሰሪያ እሳት የሚለኮሰው ደግሞ በጳጉሜን መጨረሻ ላይ ነው።
ከ12 በላይ የሆኑ የኮንታ ባህላዊ ምግቦች የሚቀርቡበት ይህ አውድ እስከ መስከረም 30 ቀን ድረስ በደማቅ ሁኔታ ይቆያል።
ፎቶዎቹንና መረጃውን ላካፈለን ኮንታ ቲዩብ ምስጋና እያቀረብን፤ እንኳን ለዘመን መለወጫው የህንግጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ሰላም ያድርግልን።
#ህንግጫ #የኮንታብሔር #ባህልእናቱፊት #አዲስዓመት #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.