#Ethiopia | የ94 ዓመቷ አዛውንት ለ24 ሰዓታት በጭቃ ስር ቆይተው በሕይወት መትረፍ ችለዋል።
በኔፓል አሰቃቂ የጎርፍ አደጋ የ94 ዓመቷ አዛውንት ከጭቃና ፍርስራሽ ውስጥ በሕይወት መትረፋቸው ተሰምቷል።
በኔፓል እና በቲቤት ድንበር አካባቢ የተከሰተው አሰቃቂ የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ በርካታ ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል።
መንደሮችና መሰረተ ልማት ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን ከ90,000 በላይ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል።
በዚህ ልብ ሰባሪ አደጋ መካከል ግን መላውን ዓለም ያስደመመ አስደናቂ የተአምር ዜና ተሰምቷል።
በአደጋው ምክንያት ሙሉ በሙሉ በወደመው የርሱዋ የአረጋውያን መንከባከብያ ማዕከል ውስጥ ይኖሩ የነበሩት የ94 ዓመቷ ጉናኬሻሪ ቦሃራ የተባሉት አዛውንት በሕይወት የተረፉ ብቸኛ ሰው ሆነዋል።
የማእከሉ ህንጻ በጎርፉ ተደርምሶ ከተወሰደ በኋላ በኑዋኮት ግዛት ለ24 ሰዓታት ያህል በከባድ ጭቃና በፍርስራሽ ስር ተቀብረው ቆይተዋል።
የነፍስ አድን ቡድኖች በከባድ ቁፋሮ ማሽኖች በመጠቀም በፍርስራሹ ስር ተቀብረው የነበሩትን አዛውንት በጥንቃቄ በማውጣት ህይወታቸውን መታደግ ችለዋል።
የእነኚህ አዛውንት በህይወት መትረፍ ለብዙዎች ተስፋ ሰጥቷል።
በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች አስክሬን እና የጠፉ ሰዎችን የመፈለጉ ስራ አሁንም በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Nepal #Tibet #flood
#Devastating #accident
#rescue #lifesaving
Source: GetuTemesgen








No comments yet.