#Ethiopia | የቡርኪና ፋሶው መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ በሀገሪቱ የሀገር ፍቅር ስልጠናን ያጠናቀቁ 65 ሺህ ወጣቶች የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
ፕሬዚዳንቱ ወጣቶቹ የሀገራቸውን ሉአላዊነት እና አንድነት ለማስጠበቅ በትጋት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በ2025 የተጀመረው የሀገር ፍቅር ስልጠና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላጠናቀቁ ተማሪዎች የሚሰጠው የሚሰጥ ነው።
ስልጠናው ለአንድ ወር ያህል ስለ ዜግነት ሀገራዊ አንድነት እና የታሪክ ትምህርቶችን እንዲወስዱ ያደርጋል።
ተማሪዎቹ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ የሚሰጣቸው የምስክር ወረቀት ዩኒቨርሲቲ ለመግባት እንደ መስፈርት ይጠየቃል።
ካፒቴን ትራውሬ ወጣቶቹ አለምን እና ጂኦፖለቲክስን በትክክል እየተረዱ የትህትና እና የሀገር ፍቅር እሴቶችን እንዲላበሱ አሳስበዋል።
ትራኦሬ በምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር “መሃይም የሆነ ሰው ለቢሊዮናችን አደጋ ነው” ብለዋል።
አክለውም “ማንኛውም አይነት ሁኔታ ቢፈጠር እራሳችሁን ልታበቁ ይገባል አቋራጭ እና ቀላል መንገዶችን አስወግዱ ምክንያቱም ያ መንገድ ወደ ክህደት ይመራል” ሲሉ ለወጣቶቹ መልእክት አስተላልፈዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#BurkinaFaso #Capitan #IbrahimTraore #Students
#Mandatory #Patriotic #Immersion #programme
Source: GetuTemesgen








No comments yet.