«ሲቢኢ – አደይ አዲስ ዓመት»

- Advertisement -
Sidebar AD

የንግድ ኤክስፖና ፌስቲቫል ተከፈተ

‎#Ethiopia | ​​በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር የተዘጋጀው “ሲቢኢ – አደይ አዲስ ዓመት ታላቅ ኤክስፖና ፌስቲቫል” የከተማዋ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የድርጅት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቆ ተከፈተ።

‎”ሁሌ አዲስ” በሚል መሪ ቃል ለአሥራ አምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ይህ ታላቅ ዝግጅት፣ ንግድን ከመዝናኛና ከባህል ክስተቶች ጋር አዋህዶ በማቅረብ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች አዲስ የበዓል ገጽታ ይዞ መጥቷል።

‎​በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ የማስተር ፒስ ትሬዲንግ ተወካይ አቶ ሄኖክ ይርጋ እንደተናገሩት፣ ድርጅታቸው በዘመናዊው አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር እንዲህ ዓይነቱን ግዙፍ ዝግጅት በማደራጀት ፈርቀዳጅ መሆን ችሏል።

‎አቶ ሄኖክ አክለውም የዝግጅቱ ዋና ዓላማ የከተማዋን ነዋሪዎች በተለይም የሰሚት፣ አያት፣ የካ አባዶና ኮተቤ አካባቢ ነዋሪዎችን ወደ መሐል ከተማ ሳይሄዱ በአቅራቢያቸው የበዓል ሸመታቸውን እንዲያከናውኑ ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።

‎ከዚህም በተጨማሪ ከተለመዱት የኤክስፖ ቦታዎች ወጣ ብሎ አዳዲስ ማዕከላትን መጠቀም የንግድና የልማት እንቅስቃሴዎችን እንደሚያቃናቸው አብራርተዋል።

‎​በዓል በመጣ ቁጥር የሚስተዋለውን የዋጋ ጭማሪ ለማቃለል የተደረገውን ጥረት አስመልከተው የማስተር ፒስ ትሬዲንግ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ በሱፍቃድ ንግግር አድርገዋል። አቶ በሱፍቃድ እንደገለጹት፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ጋር በተደረገው አጋርነት ከሁለት መቶ በላይ ነጋዴዎችና ቀጥተኛ አምራቾች በዝግጅቱ ላይ እንዲሳተፉ ተደርጓል።

‎በዚህም መሠረት እንደ ጥራጥሬ፣ ፍራፍሬ፣ እንቁላልና የወተት ተዋፅኦ ያሉ መሠረታዊ ፍጆታዎች ከመደበኛው የገበያ ዋጋ ከ15 እስከ 30 በመቶ በሚደርስ ቅናሽ ለሕዝቡ እንደሚቀርቡ ጠቁመው፣ ይህም ለበርካታ ቤተሰቦች ትልቅ እፎይታ እንደሚፈጥር አብራርተዋል።

‎​ዝግጅቱ ከግብይት ባለፈ በርካታ አዝናኝና ባህላዊ ሁነቶችን ያካተተ ነው። እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው በዚህ ፌስቲቫል ላይ የአርትና የፋሽን ትርኢቶች፣ የዳንስ ውድድሮች፣ የመጽሐፍ አውደ ርዕይ፣ የህፃናት መጫወቻዎች፣ የሳቅ ምሽት እና የክላሲክ መኪኖች ትርኢት የቀረቡ ሲሆን፣ በታላላቅ የሙዚቃ ድግሶችና ባህላዊ ትርኢቶችም እንደሚደመደም ታውቋል።

‎ጌትነት ተመስገን
‎📷 ከበደ መክብብ

‎​#AdeyExpo ​#AddisAbbaEvents ​#EthiopianNewYear ​#AdeyExpo2018 ​#AddisNewYearExpo ​#MasterpieceTrading
​#AddisInternationalConventionCenter







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2