በሕይወት እያሉ እንደሌሉ የተቆጠሩት 4.5 ሚሊዮን “ዓለም የረሳቸው” ዜጎች!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአለም ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በሕይወት እያሉ እንደሌሉ ተቆጥረው መሠረታዊ መብታቸው ተነጥቀው እንደሚገኙ መረጃዎች ጠቆሙ።

እያንዳንዱ ሰው የመኖርና የዜግነት መብቱ በዓለም አቀፍ ሕጎችና ድንጋጌዎች የተጠበቀ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይህንን መሠረታዊ መብታቸው ተነጥቀዋል ብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ቢሮ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው እነዚህ ዜጎች በሕግ ፊት ተገቢውን ዕውቅና በማጣታቸው ምክንያት በሕይወት እያሉ እንደሌሉ ተቆጥረውና ሕጋዊ ህልውና አጥተው እንዲቀሩ ተገደዋል ብሏል።

የዜግነት ማረጋገጫ ሰነድ ወይም መታወቂያ ባለመኖሩ ምክንያትም አሃዝ ውስጥ ሳይገቡ ዕውቅና ሳይሰጣቸውና ሙሉ በሙሉ በተረሱበት አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ አመላክቷል።

ይህ የዜግነት እጦት ቀውስ ግለሰቦቹ በዕለታዊ ሕይወታቸው የሚያስፈልጓቸውን መሰረታዊ ሰብአዊና ማህበራዊ መብቶች እንዳያገኙ ትልቅ ማነቆ እንደሆነባቸውም ገልጿል።

ሕጻናትና ወጣቶች ትምህርት ቤት ለመመዝገብና መደበኛ የጤና እንክብካቤ ለማግኘት ተከልክለዋል።

በሕጋዊ መንገድ ተቀጥሮ ሥራ የመሥራት፣ የባንክ ሒሳብ የመክፈትና ንብረት የማፍራት መብታቸው ተገፎ ይገኛል ሲልም ነው ተቋሙ የገለፀው።

ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ ባለመኖሩ ምክንያት በነጻነት የመንቀሳቀስ በጥበቃ ሥር በሚሆኑበት ወቅትም ተገቢውን ሕጋዊ ከለላ የማግኘት መብታቸው አጥተዋልም ብሏል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በበኩላቸው ሀገራት የዜግነት ሕጎቻቸውን በመከለስ ችግሩን ለማስወገድ የተዘጋጁ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መተግበር አለባቸው ብለዋል።

በመሆኑም ተረስተው የሚገኙ ወገኖች ወደ ሕጋዊ ሥርዓት እንዲያስገቡም ጥሪ አቅርበዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#unitednation #freedom
#Refugees #democracy
#humanrights #protection


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2