በሰራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት የስርቆት ወንጀል የፈፀመች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡

- Advertisement -
Sidebar AD

ተጠርጣሪዋ ሶሊያና አበራ ትባላለች፤ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ጣፎ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ከሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ነው።

ተጠርጣሪዋ በደላላ አማካኝት በተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት ወንጀሉን ለመፈፀም ምቹ ሁኔታን ስታጠና ነበር ያለው በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የመሪ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ የአሰሪዎቿን ከቤት ያለ መኖር በመጠቀም ከልብስ ቁም ሳጥን ውስጥ ተቀምጦ የነበረ የውግ ቁጥሩ RFLA 170306603 ፋልኮል ሪታይ ሽጉጥ ከመሰል ሦስት ጥይት ጋር እና አንድ በተን ስልክ ጋር ሰርቃ ተሰውራለች፡፡

ፖሊስም የቀረበለትን ክስ መነሻ በማድረግ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዋን ሀያ አራት ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ሲያውላት የውግ ቁጥሩ RFLA 170306603 ፋልኮል ሪታይ ሽጉጥ ከመሰል ሦስት ጥይት ጋር እና አንድ በተን ስልክ እንደተገኘባት መምሪያው አስታውቋል፡፡

የግል ተበዳይ የተሠረቀባቸው ሽጉጥ ህጋዊነትን ያረጋገጠው ፖሊስ በተጠርጣሪዋ ላይ ክስ እንደሚያስመረትባትም አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ የጦር መሳሪያን በአግባብና በጥንቃቄ መያዝ እንዳለበት ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የቤት ሰራተኞችን ሲቀጥር ተገቢው ተያዥ መኖሩን ማረጋገጥ እንደሚኖርበትም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

Addis Ababa police




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2