“በነገራችን ላይ…”

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ለረጃጅም ቃለ ምልልሶች እምብዛም ትኩረት የማልሰጥ ሰው ነኝ። ግን ብዙ ቁም ነገሮች በረጅም ቃለ ምልልሶች ውስጥ ሊገኙ እንደሚችሉ ያስተማረኝን የደረጀ ሃይሌን እና የአብነት ገብረመስቀልን ከሦስት ሰዓት በላይ የፈጀ ሁለት ክፍል ውይይት በጥሞና ተከታትያለሁ።

በእውነቱ፣ በቢዝነስና በእግር ኳስ ዓለም የሚታወቁት ሰው ግለ ታሪክ—ፈለግነውም አልፈለግነውም—“ሰው ሰው የሚሸት” ምርጥ ፕሮግራም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

የደረጀ ቃለ ምልልሶች መቼም ቢሆን ለዛና ውበት ያላቸው ሥራዎች መሆናቸው ባያጠራጥርም፣ በዚህ ቃለ ምልልስ ግን የተጠያቂውን ሙሉ Profile በማሳየት፣ ገጠመኞቹን በመንካት እና በተለያዩ ሰዎች በኩል ሲነሱ የነበሩ ሀሜቶችንና አሉባልታዎችን በማጥራት የተሳካ ሥራ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

በግሌ ከቃለ ምልልሱ የተረዳሁት፦

🔹 አቶ አብነት ከትልቅ ቤተሰብ የወጡ ሲሆን፣ በንጉሡ ዘመን “የመኮንንት ዘር” ወይም ከገዥው መደብ ወገን መሆናቸውን ቃለ ምልልሱ አጥርቶልኛል።

🔹 ከአያታቸው ኦዳ ዝርያ ጀምሮ በስፋት የተዘረጋ ቤተሰብ ያላቸው ሲሆን፣ በስፋቱ ሲታይ በኢትዮጵያዊነት መሠናሰሉ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከአነስተኛ ጎሳ የሚበልጥ ትልቅ የቤተሰብ ማኅበረሰብ እንዳላቸው ያሳያል። ምን እሳቸው ብቻ!

🔹 “ሰውየው” በቅንጡ ሕይወት ውስጥ በመሀል ቢያሳ ተወልደው ያደጉ፣ በሴንት ጆሴፍ ተምረው የጨረሱ ሲሆን፣ 18 ዓመታት በአሜሪካ በትምህርትና በሥራ ልምድ ያሳለፉ ናቸው።

🔹 ከልጅነታቸው ጀምሮ ኳስ ይጫወቱ የነበሩ እና ስለ እግር ኳስ በቂ እውቀትና ልምድ ያላቸው ሲሆን፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነታቸውም ከቤተሰብ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ግንኙነት እንደነበረው ተገልጿል።

🔹 ከዚያም ባሻገር በአሜሪካ የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ክለብ ከመሠረቱት መካከል ሲሆኑ፣ በርካታ የዘመኑን ተጫዋቾች በቅርብ የሚያውቁ ናቸው።

🔹 ከሼህ መሐመድ አልዓሙዲ ጋር በሥራና በወዳጅነት 32 ዓመታት ያሳለፉ ሲሆን፣ አሁንም በመካከላቸው አለመግባባት ቢኖር እንኳን፣ በጫወታነት ክፉ መናገር ያልፈለጉ ሰው ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።

🔹 በብዛት ለሚናፈሱ ወሬዎችና አሉባልታዎች እንደማይረቱ፣ ለአገራቸውም ሆነ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የድርሻቸውን በማበርከት የሚታወቁ ናቸው።

🔹 ለአገራችን የሕዝብ ክለቦች መዳከም ትልቁ ማነቆ፣ የፌዴሬሽኑ ሕጎች አሳሪ መሆናቸው እና ክለቦች በስቴዲየም ገቢና በደጋፊዎች መዋጮ ብቻ መፈናፈን እንደማይችሉ በማሳያ ያረጋገጡ መሆናቸውንም ተረድቻለሁ።

ከዝምታ ይልቅ፣ በተገቢው መንገድ መረጃን ለሕዝብ ማድረስ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ያየሁበት ቃለ ምልልስ ነው።

ብራቮ ደሬ!! ❤️

(ንጉሥ ወዳጅ ነን!)




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2