አሜሪካ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ተማሪዎቹን በዓድዋ ድል መታሰቢያ አስመረቀ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:- አሜሪካ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ያሰለጠናቸውን 317 ተማሪዎች በዛሬዉ እለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።

በዕለቱ ከተመረቁት ተማሪዎች መካከል 202 ወንዶች እና 115 ሴቶች ሲሆኑ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በሊደርሺፕ፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በኮምፒውተርሳይንስ የትምህርት ዘርፎች የተካተቱ መሆናቸዉ ተገልጿል።

ኮሌጁ በቅርቡ በኢትዮጵያ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን (ETA) በተደረገ የጥራት ግምገማ የመስፈርቱን መስፈርት አሟልተው ዳግም ምዝገባ ከተፈቀደላቸው ሶስት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም በቅርቡ በተካሄደው ብሔራዊ የመውጫ ፈተና የኮሌጁ ተማሪዎች በኮምፒዩተር ሳይንስ 72% እንዲሁም በቢዝነስ አስተዳደር80% የማለፍ ውጤት ማስመዝገባቸው ተብራርቷል።

ኮሌጁ ባከናወናቸው የማህበራዊ ሀላፊነት ስራዎች ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ550 ሺህ በላይ ወጣቶችን አጭር ስልጠና በመስጠት ከ120 ሺህ በላይ ለሚሆኑት የስራ እድል መፍጠሩ ተመልክቷል።

ወደፊትም በሚቀጥሉት 4 ዓመታት ከ3 ሚሊዮን በላይ ሴቶችንና ወጣቶችን ለማሰልጠን እና 2 ሚሊዮን የሚሆኑትን የስራ እድል ለመፍጠር የሚያስችል ፕሮጀክት ከአለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር እየሰራ እንደሚገኝ ነዉ የተገለፀዉ።

ተማሪዎች በቡድን በመደራጀት የራሳቸዉን የሶፍትዌር ልማት እንዲመሰርቱና ወደ ስራዉ አለም እንዲቀላቀሉ የሚያበረታታዉ እና ብቁ የሚያደርገዉ ይህ ኮሌጅ ዲጂታል 2030ን ታሳቢ በማድረግ የአርቲፊሻል ኢንተልጀንሲ (AI) የትምህርት ፕሮግራሞችን ለመጀመር ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑ ተገልጿል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: