አምባሳደር አሚን አብዱልቃድር በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ የእውቅና ሽልማት ተቀበሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱት አምባሳደር አሚን አብዱልቃድር የተዘጋጀላቸውን የእውቅና ሽልማት ተቀብለዋል።

አምባሳደር አሚን በሀገራችን የሆቴልና ቱሪዝም መስክ ውስጥ ያከናወኗቸውን አበይት ተግባራት አከናውነናል።

አምባሳደር አሚን ለአዳዲስ አሰራሮችና ለላቀ ለውጥ ያላቸው ፍላጎት፣ ከሀገር ፍቅርና ከተግባቢ ባህሪያቸው ጋር ተይዞ የተዋጣላቸው ሀገራዊ መሪ አድርጓቸዋል።

በሚኒስትርነት ማዕረግ ሀገራቸውን ባገለገሉበት ወቅት ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ አድርገው በማንሳትና አዎንታዊ ገጽታዋን በመገንባት ረገድ ፈር ቀዳጅ ሚና ተወጥተዋል።

ታዋቂ የኪነ ጥበብ ሰዎችን፣ የሃይማኖት አባቶችን እና ታዋቂ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ አካላትን አስተባብረው በመምራት ኢትዮጵያን ለዓለም አስተዋውቀዋል።

ይህ ጥበብ የተሞላበት አመራራቸው የኢትዮጵያ ባህል፣ ቅርስና የቱሪዝም ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥበብና በክብር እንዲንፀባረቅ አድርጓል።

የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ፈር ቀዳጅ፡ በኢትዮጵያ የሆቴል ዘርፍ ታሪክ የመጀመሪያውን የሆቴሎች ደረጃ ምደባና የመታወቂያ አሰራር በማስፋፋት የአገልግሎት ጥራት በዘመናዊ መለኪያ እንዲመራ መሠረት ጥለዋል።

ዘርፉን ወደ ሙያዊነት ማሸጋገር፡ በተለምዶ ይካሄድ የነበረውን አሰራር በመቀየር ዘርፉ በሙያዊነትና በጥራት እንዲመራ በማድረግ ለብዙ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል።

የሰው ኃይል አቅም ግንባታ፡ ከመላ ሀገሪቱ የተመረጡ ባለሙያዎችን ለአንድ ዓመት ሙሉ በማሰልጠን የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉን በሰለጠነ የሰው ኃይል የማጠናከር ሥራ ሰርተዋል።

የኢትዮጵያ የቱሪዝም ብራንድ ማዘመን፡ ሀገራችን ለዘመናት ትጠቀምበት የነበረውን “13 Months of Sunshine” የሚለውን መለያ ወደ አዲሱ “Land of Origins” በማሸጋገር የኢትዮጵያን የቱሪዝም ምስል በዓለም አቀፍ ደረጃ አድሰዋል።

ተቋማዊ መዋቅሮችን መገንባት፡ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ካውንስል፣ የቱሪዝም ቦርድ እና የቱሪዝም ድርጅት እንዲመሰረቱ በማድረግ ዘርፉ ጠንካራ ተቋማዊ መሠረት እንዲይዝ አድርገዋል።

የትምህርትና ስልጠና ሥርዓትን ማጠናከር፡ በሙያ ትምህርትና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የባህልና ቱሪዝም ትምህርት ኮርሶች እንዲዘጋጁ በማድረግ ለዘርፉ ማደግ ወሳኝ የሆነውን የሰው ኃይል ማፍሪያ መንገድ ቀይሰዋል።

ለቅርሶችና ተፈጥሮ ሀብት ሕጋዊ ጥበቃ ማድረግ፡ ፓርኮች፣ ጥብቅ ቦታዎችና የቅርስ ሥፍራዎች በሕግ እንዲከለሉና በፓርላማ በይፋ እንዲታወጁ በማድረግ የሀገር ሀብት ለትውልድ እንዲተላለፍ አስችለዋል።

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ማደስ፡ ፓርኩ ከአደጋ ዝርዝር እንዲወጣ ለ5 ዓመታት የተዘረጉ ጥብቅ የአመራር፣ የጥበቃና የሕግ መስፈርቶችን በብቃት በማስተባበር ውጤት አምጥተዋል።

የማይዳሰሱ ቅርሶችን በዩኔስኮ ማስመዝገብ፡ ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ኮሚቴ ውስጥ በአመራርነት እንድትሳተፍ ከማድረግ ባሻገር የመስቀል፣ የቻምበላላ፣ የገዳ ሥርዓት እና የጥምቀት በዓላት በዓለም አቀፍ የማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ እንዲመዘገቡ በማድረግ ታሪካዊ አሻራ አኑረዋል።

እነዚህ አበርክቶዎች ለሀገራችን የሆቴል፣ የቱሪዝም፣ የባህልና የቅርስ ዘርፎች የተጣሉ ዘላቂ ተቋማዊ መሠረቶች ናቸው።

ክቡር አምባሳደር አሚን ለሀገራቸው ላሳዩት ፍቅር፣ የለውጥ አርበኝነትና ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል።

እንኳን ደስ አልዎት።

#EthiopianTourism #HotelAndTourism #CultureAndHeritage #AmbassadorAmin #LandOfOrigins #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2