#Ethiopia | ለረጅም ጊዜ ለአገልግሎት ሲያውል የነበረው የአድዋ ድልድይ በመጎዳቱ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለማስቀረት ሲባል መንገዱ ለአሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ገለጸ።
በድልድዩ ላይ ለተከሰተው ክፍተት በጥናትና በዲዛይን የተደገፈ አስተማማኝ መፍትሔ እስከሚበጅለት ድረስ፣ ከሴቶች አደባባይ ወደ ባልደራስ ትራፊክ መብራት የሚያመራው መስመር ከዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪዎች ዝግ መሆኑ ተመልክቷል።
በመሆኑም አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለሥልጣኑ ጥሪ አቅርቧል።
#AdwaBridge #AddisAbabaRoads #TrafficUpdate #EthiopiaRoads #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen







No comments yet.