በኔፓል የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ1,000 በላይ መድረሱ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

በኔፓል በተከሰተው ከባድ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 1,003 መድረሱን የአገሪቱ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ባለስልጣን አስታወቀዋል።

ባለስልጣኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ከሟቾቹ በተጨማሪ በርካታ ሰዎች የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የነፍስ አድን ሰራተኞች አሁንም አስከሬኖችን ፍለጋ እና በጎርፍ የተከበቡ ሰዎችን የማውጣት ስራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

በጎርፉ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በመሰረተ ልማቶችና በመኖሪያ ቤቶች ላይም ከፍተኛ ውድመት መድረሱ ተገልጿል።

የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ባለስልጣኑ የሟቾች ቁጥር አሁንም ሊጨምር እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።

ልዑል ወልዴ



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1