በጥርስ ሕክምና የላቀ አፈጻጸም ላላቸው ተቋማትና ባለሙያዎች እውቅና ሊሰጥ ነው!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja I በጥርስ ሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የሕክምና ተቋማትና ባለሙያዎች እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ አዲስ የሽልማት መርሃ-ግብር በዛሬዉ እለት በሳፋየር አዲስ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ይፋ ተደርጓል።

መርሃ-ግብሩ በአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን (AAFDA) እና በሮባ መልቲ ሚድያና ኢቬንትስ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ትግበራው በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት 2019 ዓ.ም እንደሚከናወን ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሙሉእመቤት ታደሰ እንደገለጹት፤ መርሃ-ግብሩ በህግ ከተሰጣቸው ቁጥጥርና ፈቃድ የመስጠት ኃላፊነት ባሻገር፣ ጥራታቸውን ጠብቀው የሚሰሩ የጤና ተቋማትን በማበረታታት ለአገልግሎት ተቀባዩ ማህበረሰብ የተሻለ የጤና ዋስትና ለመስጠት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።

አክለውም፣ መርሃ-ግብሩ የጥርስ ሕክምና ማዕከላትን አቅም በመገንባት፣ የልምድና የዕውቀት ሽግግር በመፍጠር እንዲሁም የሀገሪቱን የሕክምና ቱሪዝም (Medical Tourism) በማሳደግ አዲስ አበባን በአፍሪካ የጥርስ ሕክምና ማዕከል ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።

አሸናፊዎች የሚለዩባቸው ዋና ዋና የምዘና መስፈርቶች፦የባለስልጣኑ ሙያዊ ምዘና (70%)፦ በኢትዮጵያ ስታንዳርድ ኤጀንሲ መስፈርት መሰረት ተመዝነው 75% እና ከዚያ በላይ ያገኙ ተቋማት የሚካተቱ ሲሆን ሌላኛዉ
የሕዝብና የደንበኞች ድምፅ (30%)፦ አገልግሎት በሚያገኙ ደንበኞች የቀጥታ ድምፅ (Vote) እንደሚወሰንም ነዉ የተገለፀዉ።

በአጠቃላይ በ15 የሙያ ዘርፎች እውቅና የሚሰጥ ሲሆን፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ በኢንፌክሽን ቁጥጥር፣ ለህጻናትና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አካባቢ በመፍጠር፣ በኮስሞቲክ ሕክምና፣ በላቦራቶሪ ብቃት ፣በማህበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ተቋማትና ባለሙያዎች የሚሸለሙ ይሆናል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ የእውቅና መርሃ-ግብር በየዓመቱ ደረጃውን ጠብቆ የሚቀጥል ሲሆን፣ የውድድሩን ሂደትና መረጃዎች ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ይፋዊ ድህረገጽ እና የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች መከፈታቸው ተገልጿል።

#ኹነት






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: