በዓለም የነዳጅ ማጓጓዣ ቁልፍ መስመር በሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ ሁለት ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በድብቅ ጥቃት መመታታቸውን የባህር ላይ ደህንነት አማካሪ ድርጅቶች አስታዉቀዋል።
ማሪስክስ የተባለው የባህር ላይ ደህንነት አማካሪ ድርጅት እንደገለጸው፤ የሳውዲ አረቢያው “ባህሪ” ማጓጓዣ ኩባንያ ባለቤትነት የሆነው “ሲድር” እና “በሲኖኮር” የሚተዳደረው “ሴኔጋል ፕሮስፔሪቲ” የተባሉ ሁለት ግዙፍ የነዳጅ መርከቦች ፋርስ ሰርጥን ለቀው በመውጣት ላይ እያሉ በማይታወቁ ፕሮጀክታሎች ተመተዋል።
የብሪታንያ የባህር ላይ ንግድ ክዋኔ በበኩሉ፣ አንደኛው መርከብ ከኦማን የባህር ጠረፍ ውጪ ጉዞውን በማጠናቀቅ ላይ በነበረበት ወቅት በሦስት ጥቃቶች መጎዳቱን አረጋግጧል። በተከሰተው አደጋ እስካሁን በሁለቱም ኩባንያዎች በኩል ይፋዊ ምላሽ ያልተሰጠ ሲሆን፣ ጥቃቱ በቀጣናው የነዳጅ ማጓጓዣ መርከቦች ደህንነት ላይ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ ተመልክቷል።
Source: Yeneta Tube








No comments yet.