#Ethiopia | አንድ ልብ አንድ ሐሳብ ለተናበበ የቤተክርስቲያን አገልግሎት በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የማኅበረ ቅዱሳን 17ኛው ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት የተጣጡ ከ800 በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።
የማኅበሩ ሰብሳቢ አቶ ካሳሁን ኃይለማርያም በስብሰባው መክፈቻ ላይ እንዳመለከቱት፣ ማኅበሩ ከተመሠረተበት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት 34 ዓመታት መዋቅሩን በማስፋፋት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በርካታ ማእከላትን፣ ግንኙነት ጣቢያዎችን እና 481 ግቢ ጉባኤያትን በማቋቋም አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል።
በግቢ ጉባኤያት በኩል ከ100 ሺህ በላይ ተማሪዎችን የሚያስተምረው ማኅበሩ፣ በ2017 እና 2018 ዓ.ም ብቻ 332 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የዩኒቨርሲቲ ዋንጫ እና ሜዳሊያ ተሸላሚ እንዲሆኑ አግዟል።
በተጨማሪም ባለፉት ሁለት ዓመታት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ከ103 ሺህ በላይ አዳዲስ ምእመናን ማጥመቅ መቻሉን፣ ለአይነ ስውራን በብሬይል የተዘጋጀ የነገረ ድኅነት ቡክሌት ማሰራጨቱን፣ እንዲሁም በበርካታ ቋንቋዎች ከ300 በላይ መዝሙራትና 120 መጻሕፍትን ማዘጋጀቱን ሰብሳቢው ገልጸዋል።
ለአብነት ትምህርት ቤቶች መምህራንና ደቀ መዛሙርት ከ27.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወርኃዊ ድጎማ የተደረገ ሲሆን፣ 76 የቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ዲዛይኖችን በነጻ በመስራት ከ97.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን ተችሏል።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን ጨምሮ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና ጥሪ የተደረገላቸው አባቶች ተገኝተው አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል።
ጉባኤው በቀጣይም የቤተክርስቲያኗን ወቅታዊ ሁኔታዎች በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
#የማኅበረቅዱሳንጉባኤ #ማኅበረቅዱሳን #ቤተክርስቲያን #የኢትዮጵያኦርቶዶክስ #ግቢጉባኤ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen







No comments yet.