ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ በፒያሳ አዲስ ሾውሩም በማስመረቅ አዶናይ ብርሃኔን የብራንድ አምባሳደር አደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ በአዲስ አበባ ፒያሳ ከኤሊያና ሆቴል አጠገብ ያዘጋጀውን አዲስ ሾውሩም በይፋ ያስመረቀ ሲሆን፣ ታዋቂውን የቲክቶክ ይዘት ፈጣሪ አዶናይ ብርሃኔን ለስድስት ወራት የሚቆይ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሰይሟል።

በኤሌክትሮኒክስ ንግድ ዘርፍ ከ10 ዓመታት በላይ የዘለቀ ልምድ ያለው ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ፣ በፒያሳ ከኤሊያና ሆቴል ጎን የከፈተው አዲስ ሾውሩም ደንበኞች ጥራታቸውን የጠበቁ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን በቀላሉ እንዲያወዳድሩ እና በዘመናዊ መንገድ እንዲገበያዩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ተቋሙ የምረቃ ስነ-ስርዓቱን አስመልካች በዲጂታል ማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ተፅዕኖ ካላቸው ወጣቶች አንዱ የሆነውን አዶናይ ብርሃኔን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መስየሙን ይፋ አድርጓል።

አዶናይ ብርሃኔ በመዝናኛ ዘርፍ በሚፈጥራቸው ይዘቶች ከማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቹ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት ያለው ሲሆን፣ በችግር ውስጥ ላሉ ወገኖች በሚያደርገው ድጋፍና ድምፅ የመሆን ማህበራዊ ተሳትፎው ይታወቃል። ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ ይህንን የወጣቱን አዎንታዊ ተፅዕኖ በመንተራስ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በዲጂታል ይዘቶች፣ በማስተዋወቂያ ዘመቻዎች እና በብራንድ እንቅስቃሴዎች አብረው ለመስራት መወከናቸውን አስታውቋል።
ድርጅቱ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ጥራት ያላቸውን የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች በማስመጣት ከሚያደርገው የንግድ እንቅስቃሴ ጎን ለጎን፣ የእርዳታ ድርጅቶችን በመደገፍ፣ የማዕድ ማጋራት እና የተማሪዎች ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የሚታወቅ ተቋም ነው። ይህ አዲሱ የሾውሩም ምረቃ እና የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነት ተቋሙ አሰራሩን ከዘመናዊው የዲጂታል ገበያ አሰራር ጋር ለማጣመር የያዘውን አቅጣጫ የሚያሳይ መሆኑ ተገልጻል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2