እሁድ ጷግሜ 1 2018 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ዝግጅት ላይ በሥራቸው ስኬታማ በመሆን ለሌሎች ሴቶች ምሳሌ መሆን ለቻሉ ሴቶች የዕውቅና የምስጋና ሽልማትና ሰርተፊኬት ይበረከትላቸዋል፡፡
“ዕንቁ ሴት- ንቁ ሴት” ሽልማት ከዚህ ቀደም ለ8 ጊዜ ያህል የተካሄደ ሲሆን ደራሲት የዝና ወርቁ ፣ ደራሲት ሜሪ ጃዕፋር፣ ደራሲት ውዳላት ገዳሙ፣ አርቲስት መቅደስ ጸጋዬ ፣ በረከት ወርቁ(በረከት ገበሬዋ)፣ ዲዛይነር ሳራ መሐመድ፣ ሜንቶር ፍጹም ኪዳነማርያም፣ ጨምሮ ከ 20 በላይ ለሆኑ ተምሳሌት ሴቶች የዕውቅና ሽልማት እንደተበረከተላቸው ታውቋል።
ጳጉሜ 1 ከቀኑ 7:00 ጀምሮ
በዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ (ፒያሳ ቴድሮስ አደባባይ መርሀ ግብሩ የሚደረግ ሲሆን ታላላቅ እንግዶችም ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘንድሮ በሚደረገው የእውቅና ሽልማት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን፣የቻለ ማሞ፣መካነ ሰላምመሐመድ እና ቲና ተረፈ፣መስከረም አሰግድ፣ሰናይት በዙ፣ ፍሬህይወት ታምሩ፣ ፅላት ገዝሙ እና ገነት ከበደ (አቢሲያኒያ) እውቅና እንደሚያገኙ ታውቋል። ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ የበላይ ጠባቂ የሆኑበት ይህ የሽልማት መርሀ ግብር ላይ ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ እና ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ንግግር ያደርጋሉ።
ዕንቁ ኤቨንትስና ሳሜሎስ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን በጋራ የሚያዘጋጁት “ዕንቁ ሴት – ንቁ ሴት” የዕውቅና ሽልማት ወደፊትም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል የሽልማቱ ሀሣብ አመንጪ እና መሥራች አቶ ሳሙኤል ገረመው ይናገራሉ።
የእውቅና ሥነ-ሥርዓቱ የሚድያ ማስተባበርና የሕይወት ታሪክ ማጠናከር ዝግጅቱ በተወዳጅ ሚድያ የሚከናወን ነው።
Source: FastMereja









No comments yet.