ከ48.1 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን የካፒታል በጀት የተገነባው ድልድይ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ።በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ …

- Advertisement -
Sidebar AD
ከ48.1 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን የካፒታል በጀት የተገነባው ድልድይ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ።
በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ ለዘመናት የነበረውን የትራንስፖርት እንግልት የሚቀርፍና በርካታ ቀበሌዎችን እርስ በእርስ የሚያስተሳስር የ48 ሜትር ርዝመት ያለው የሳልሜኔ ወንዝ የኮንክሬት ድልድይ ግንባታ በሙሉ ጥራትና በፍጥነት መጠናቀቁ ተበሰረ።
የአማራ ክልል መንግስት በመደበው ከ48.1 ሚሊዮን ብር በላይ የካፒታል በጀት የተገነባው ይህ መሰረተ ልማት፣ አልብኮ ከተማን ከደጋጋ እና ነጢ ቀጠናዎች ጋር በማገናኘት የ9 ቀበሌዎች ነዋሪዎችን የቀን ተቀን እንቅስቃሴ የሚያቃልል ሆኗል።
የድልድዩ መጠናቀቅ ለአካባቢው ያመጣቸውን ዋና ዋና ጥቅሞች በጥቅሉ ሲቃኙ፦
• በአካባቢው የሚመረቱ የግብርና ምርቶች ወደ ገበያ የሚቀርቡበትን መንገድ ከማስፋቱ በላይ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ያጠናክራል።
• በየዓመቱ ታላቁ የመውሊድ በዓል በድምቀት የሚከበርበትን ታሪካዊውን የጀማል ንጉስ መስጅድ ለመጎብኘት ለሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር እንግዶች ምቹ የትራንስፖርት አማራጭ ይፈጥራል።
• የወረዳው መዲና ለሆነችው አልብኮ ከተማ ተጨማሪ ውበት በመስጠት የኢንቨስትመንትና የከተማዋን ፈጣን እድገት ያፋጥናል።
ለዚህ ፕሮጀክት ስኬታማነት የዞኑና የወረዳው አስተዳደር አካላት ላደረጉት የቅርብ ክትትል፣ ስራውን በጥራት ላጠናቀቀው የወጣት ምሩቃን ኢንተርፕራይዝ ስራ ተቋራጭ እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ላሳየው ያልተቋረጠ ትብብር ከፍተኛ ምስጋና ተቸርቷል።
©️ደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: