የ5 ዓመት ታዳጊን 10 ሜትር ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ውስጥ የጣ ለች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውላለች

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ 02 ቀበሌ ከወላጆች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት የ5 ዓመት ታዳጊን 10 ሜትር ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ውስጥ የጣ ለች ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏ ተገለጸ።

​እንደ ዋቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ደነቀ ዳኜ ገለጻ፣ ድርጊቱ የተፈጸመው ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት አካባቢ ልዩ ስሙ ሆስፒታል ሰፈር በተባለ ቦታ ነው። ተጠርጣሪዋ ታዳጊዋ ከልጆቿ ጋር እየተጫወተች በነበረበት ወቅት ከወላጆቿ ጋር በነበራት ጥል ምክንያት ነጥላ በመውሰድ 10 ሜትር ጥልቀት ባለው የውሃ ጉድጓድ ውስጥ በመጣል ወደ ቤቷ መግባቷ ተነግሯል።

​የታዳጊዋ ወላጆችና የአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉት አሰሳ፣ ህጻኗ ከጉድጓዱ ውስጥ ባሰማችው ለቅሶ ከምሽቱ 2:30 ሰዓት ገደማ ልትገኝ ችላለች። የፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የተቀናጀ የረድኤት ጥረት ታዳጊዋን ከጉድጓዱ ውስጥ በህይወት ማውጣት ተችሏል።

​ወዲያውኑ ወደ ዋቻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመውሰድ አስፈላጊው የህክምና እርዳታ እንዲደረግላት ከተደረገ በኋላ በጤናማ ሁኔታ ከቤተሰቦቿ ጋር እንድትቀላቀል ተደርጓል። ድርጊቱን ፈጽማለች የተባለችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተካሄደባት እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ወላጆችም የልጆቻቸውን ውሎና እንቅስቃሴ በቅርበት እንዲከታተሉ ፖሊስ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: