#Ethiopia | የእግር ኳስ ምልክቱ አርጀንቲናዊው ኮኮብ ሊዮሌል ሜሲ ከሚወደው ኳስ ሊሰናበት መሆኑን አሳወቀ።
ይህ ከኮከቡ የተሰማ ቃል የእግር ኳስ አድናቂዎችን በስሜት እንዲወድቁ ያደረገ ዜና ነው።
እግር ኳስን የራሱን ቋንቋ ያስተማረው የዘመናችን የእግር ኳሱ ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ በመጨረሻም ከሚወደው ኳስ ጋር የሚለያይበትን ጊዜ ይፋ አደረገ።
ይህ ከኮከቡ የተሰማ ልብ የሚነካ ዜና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የእግር ኳስ አድናቂዎችን በከፍተኛ ስሜትና እምባ ውስጥ ጥሏል።
እግር ኳስን የራሱን ቋንቋ ያስተማረው ሜዳ ውስጥ በተአምራዊ ክህሎቱ ተቃዋሚዎችን ብቻ ሳይሆን መላውን ዓለም ማስደመም ችሏል።
ሜሲ የመጨረሻውን ምዕራፍ ለመዝጋት መወሰኑን ሲናገር የእግር ኳሱ ዓለም ጥልቅ ህመም እና ቁዘማ ውስጥ ገብቷል።
በተጫዋችነት ዘመኑ ስምንት የባሎንዶር (Ballon d’Or) ሽልማቶችን በማግኘት ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ቻምፒዮን በመሆን እንዲሁም በክለብ ደረጃ የቻምፒዮንስ ሊግ እና የሊግ ዋንጫዎችን በመሰብሰብ የማይደገም ታሪክ ፅፏል።
ይህ ድቅድቅ ኮከብ ከሜዳ ውጪ የሚሆንበት ቀን መቃረቡን ይፋ ማድረጉ አጠቃላይ የስፖርቱን አየር ሁኔታ ቀይሮታል።
ብዙዎች “የእግር ኳስ ዘመን አበቃ” እስከማለት ደርሰዋል።
የሜሲ ደጋፊዎች የቡድን አጋሮቹ እና የቀድሞ ተፎካካሪዎቹ ሳይቀሩ ለዚህ ታላቅ ተጫዋች ያላቸውን አክብሮት እና የጽኑ ፍቅር መግለጫዎችን በመልቀቅ ላይ ይገኛሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Lionelmessi #Argentina
#Retirement #football
#Fans #skills #Barcelona
Source: GetuTemesgen









No comments yet.