#Ethiopia | በሰሜናዊ ቆጵሮስ የባህር ዳርቻ 267 ሰዎችን አቃፊ የነበረች የመንገደኞች ጀልባ በመስመጧ ቢያንስ የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን የ 18 ሰዎች ደግሞ አሁንም የደረሱበት አልታወቀም።
ፊሎ ጄት በመባል የምትታወቀው እና 259 መንገደኞችን እንዲሁም 8 የሰራተኛ አባላትን የያዘችው ይህች ጀልባ ከኪሬኒያ ወደ ቱርክ ታሱቹ የምታደርገውን ጉዞ እንደጀመረች በገጠማት ከፍተኛ ማዕበል ምክንያት በውሃ በመሞላቷ ተገልብጣ ሙሉ በሙሉ ወደ ባህር ሰጥማለች።
አደጋውን ተከትሎ በቱርክ እና በሰሜናዊ ቆጵሮስ አየር እና ባህር ኃይሎች አማካኝነት በተካሄደው አፋጣኝ የነፍስ አድኖ ስራ ከ 240 በላይ ሰዎች በህይወት መታደግ ተችሏል።
የአካባቢው ባለስልጣናት በአደጋው ምክንያት የሦስት ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን ያወጁ ሲሆን፣ የአደጋውን መንስኤ የማጣራት ስራ መጀመሩን እና የጀልባዋ ካፕቴንን ጨምሮ ስምንት የሰራተኛ አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
#NorthernCyprus #Shipwreck #MaritimeDisaster #Mediterranean #RescueOperation #GlobalNews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.