የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ5 ዓመታት 19.04 ሚሊዮን የሥራ ዕድሎችን መፍጠሩን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ የ5 ዓመት አፈጻጸሙን በገመገመበት መድረክ፣ ከ19.58 ሚሊዮን የሥራ ዕድል ዕቅድ ውስጥ 19.04 ሚሊዮን በማስመዝገብ 97.22 በመቶ አፈጻጸም መገኘቱን ገልጿል።
በተጨማሪም የገበያ ትስስር 116 በመቶ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ደግሞ 167.26 በመቶ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በመድረኩ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የክህሎት ልማት እና የአሠሪ–ሠራተኛ ጉዳዮች አፈጻጸም የቀረቡ ሲሆን፣ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ምርቶች ኤግዚቢሽንም በአዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር ለሦስት ቀናት ተዘጋጅቷል።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው የኤግዚቢሽኑ ዓላማ በሥራና ክህሎት ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን ለማሳየት፣ የተገኙ ተሞክሮዎችን ለመጋራት እና በዘርፉ የታዩ ተግዳሮቶችን ለይቶ ለቀጣይ ሥራ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው።
በመድረኩም የሥራ ፈጠራን ማስፋፋት፣ የወጣቶችን ክህሎት ማሳደግ እና የሠራተኛውን በሥራ ገበያ ተወዳዳሪነት ማጠናከር ላይ ቀጣይ ትኩረት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
addisreporter2
Source: Yeneta Tube









No comments yet.