‎“አዲሱ የዓለም ሥርዓት” የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​በዓለም አቀፍ አስተዳደር፣ በእኩልነት እና በሀብት ክፍፍል ዙሪያ አዳዲስና የተለዩ ፍልስፍናዊ ሀሳቦችን ያካተተው “አዲሱ የዓለም ሥርዓት” የተሰኘ መጽሐፍ በይፋ ተመረቀ።

‎​በ340 ገጾች የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ፣ በዓለም ላይ የሕዝቦች እኩልነት፣ ፍትሕና ወንድማማችነት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲሰፍን የዓለም አስተዳደር በአዲስ አስተሳሰብ ሊቃኝ ይገባል የሚል ጠንካራ ሞጋች ሀሳብን ያነሳል።

‎መጽሐፉ ይህ አስተሳሰብ በምን መልኩ ወደ ተግባር ሊለወጥ እንደሚችል ከኢኮኖሚ፣ ከመልክዓ ምድር፣ ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከሃይማኖት፣ ከባህልና ከማህበራዊ ጉዳዮች አንጻር በስፋት ዳስሶ ያቀርባል።

‎​በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰርፀፍሬ ስብሀት፣ እንደዚህ ያሉ አዳዲስ ሀሳቦች የምርምር አስተሳሰብን ለማሳደግና ለሀገር ግንባታ አዳዲስ አማራጮችን ለማፍራት ያላቸውን ትልቅ ሚና ገልጸዋል።

‎በተመሳሳይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ገዛኸኝ ፀጋው በበኩላቸው፣ መጽሐፉ በአቀራረቡ የተለየና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊወያዩበት የሚችሉ ፍልስፍናዊ ሀሳቦችን ያካተተ መሆኑን አብራርተዋል።

‎​ይህ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ የቀረበው “አዲሱ የዓለም ሥርዓት” መጽሐፍ፣ ሀሳቡ ከኢትዮጵያ አልፎ ለዓለም አቀፍ አንባቢያን እንዲደርስ በተጨማሪ ወደ 13 ቋንቋዎች መተርጎሙም ተገልጻል።

‎Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ
‎#NewWorldOrder Book Launch
‎​#TadeleDriba ​#EthiopianLiterature
‎​#BookLaunchEthiopia ​#WorldGovernment
‎​#GlobalGovernance







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1