#Ethiopia | ቻይና በቅርጹ ቦምብ ጣይ የሚመስል ግዙፉ የመንገደኛ አውሮፕላን አስተዋወቀች።
ባለሙያዎች ይህ ፈጠራ የዓለምን አቪዬሽን የሚያንቀጠቅጥ ድንቅ ፈጠራ ብለውታል።
ቻይና ከ800 በላይ መንገደኞችን ማጓጓዝ የሚችል አዲስ የሲቪል አውሮፕላን ንድፍ ይፋ አደረገች።
ይህ የወደፊት የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው አውሮፕላን ከተለመዱት የሲቪል አውሮፕላኖች ይልቅ ቅርጹ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን የሚመስል ነው።
ንድፍ እንደሚያሳየው የአውሮፕላኑ ጎን ለጎን ስፋት 85 ሜትር ገደማ ሲሆን ይህም የአሜሪካውን B-2 ስፒሪት የጦር አውሮፕላን ስፋት በ1.6 እጥፍ ያህል ይበልጠዋል ተብሏል።
ልዩ ኤሮዳይናሚክ ቅርጹ በአየር ላይ የሚፈጠረውን ግጭት በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ የነዳጅ አጠቃቀሙም ዝቅተኛ መሆኑ ተነግሯል።
ሙሉ አውሮፕላኑ መቼ ተሰርቶ እንደሚያልቅ ወይም ለአገልግሎት እንደሚበቃ እስካሁን ይፋ የተደረገ የጊዜ ሰሌዳ የለም።
ነገር ግን ፕሮጀክቱ ከተሳካ በአቪዬሽን ታሪክ ውስጥ ከተሰሩት ትልልቅና አስደናቂ የመንገደኛ አውሮፕላኖች አንዱ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#China #technology
#physics #Airplane
#Newtechnology
Source: GetuTemesgen









No comments yet.