#Ethiopia | የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ እና የሀገሪቱ የጦር ኃይሎች አዛዥ የሆኑት ጄነራል ሙሁዚ ካይነሩጋባ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሯቸው የጎሳ ማንነትን ማዕከል ያደረጉ ጽሑፎች ሳቢያ ከሩዋንዳ መንግሥት ጥብቅ ተቃውሞ እና ውግዘት ገጠማቸው።
የሩዋንዳ መንግሥት የጄነራሉን ንግግሮች “የጎሳ ፅንፈኝነት” ሲል የኮነነ ሲሆን ክስተቱ በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል አዲስ የዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ተነስቷል።
በተጨማሪም ጄነራሉ በሌላ መልዕክታቸው የሩዋንዳውን ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜን “እስካሁን ካገኘኋቸው ቱትሲዎች መካከል እጅግ አደገኛው” ሲሉ የገለጿቸው ሲሆን ይህም በዲፕሎማሲያዊ እና በማህበራዊ መድረኮች ላይ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።
ለእነዚህ አስተያየቶች ምላሽ የሰጡት የሩዋንዳ መንግሥት ቃል አቀባይ ዮላንዴ ማኮሎ ሀገራቸው ከእ.ኤ.አ 1994ቱ የዘር ማጥፋት እልቂት በኋላ የህዝቦቿን አንድነት ለማስጠበቅና ለማነጽ ለበርካታ አስርት ዓመታት ስትጥር መቆየቷን አስታውሰዋል።
ቃል አቀባይዋ አክለውም የጄነራል ሙሁዚ ንግግሮች ይህንን ሀገራዊ አንድነት የሚሸረሽሩና የጎሳ ክፍፍልን የሚያበረታቱ በመሆናቸው በፍጹም ተቀባይነት የሌላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።
ይህ የሩዋንዳ መንግሥት ይፋዊ ኮነኔ የመጣው አንድ የኡጋንዳ ጠበቃ ጄነራሉ የሁቱ እና የቱትሲ ማንነቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተደጋጋሚ ማንሳታቸው ለሩዋንዳውያን ምቾት የሚነሳ መሆኑን በአደባባይ በጥያቄ መልክ ካቀረቡ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.