#Ethiopia | በሚስ ወርልድ የዓለም ዲዛይነሮች ውድድር ላይ የቀረበችው የኡጋንዳ ተወካይ በፋሽን መድረክ ላይ የተለመዱ ውበቶችን ብቻ ሳይሆን የተለየና ጥልቅ የሆነ ሰብአዊ ታሪክ ይዛ በመቅረብ የብዙዎችን ቀልብ ስባለች።
“ኪሻ” በተሰኘው የኡጋንዳ የፋሽን ዲዛይን ተቋም የተቀረፀው ይህ ቀሚስ አንዲት እናት ለመውለድ ስለምታደርገው ቀዶ-ሕክምና ወቅት የምታልፍበትን አካላዊና መስዋዕትነት የተሞላበት ጉዞ ደረጃ በደረጃ የሚያሳይ አሰራር አለው።
ይህ አልባሳት ከስብና ፋሺያ ንብርብር ተነስቶ ወደ ጡንቻ፣ በመቀጠልም የሆድ ዕቃ ሽፋን ፣ ማህፀን እና በመጨረሻም የፅንስ ከረጢት ድረስ ያሉትን የህክምና እና የአካላዊ ሁኔታ በጥበብ ያሳያል።
የቀሚሱ የጨርቅ ቀለም ከፒችና ወርቃማ ቀለሞች ተነስቶ ደረጃ በደረጃ ወደ ኮራል፣ ቀይ፣ ማሩን እና ጥቁራማ ቀይ የሚቀያየር ሲሆን፣ ይህም እናቶች ከፅንስ እንክብካቤ እስከ ልጅ መውለድ ድረስ የሚያልፉበትን ጥልቅ ስሜታዊ ሂደት እና የህይወት መፈጠር ጉዞን በግልጽ ይገልጻል።
በተጨማሪም በሜርሜይድ ቅርፅ በተሰራውና ንብርብር በሆኑት የቱል ጨርቆች ላይ በጥንቃቄ የተረበቡት ሉሎች፣ የብርጭቆ ዶቃዎች እና ክሪስታሎች በእያንዳንዱ የልብሱ ክፍሎች ላይ ጥልቀትና ልዩ ውበት በመስጠት የፅንስ ጉዞውን በእይታ የተሞላ አድርገውታ።
ይህ የፈጠራ ስራ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እናቶች የሚያልፉበትን ጥልቅ የእናትነት ተሞክሮ በዓለማችን የውበት መድረክ ላይ የሚለበስ የጥበብ ስራ አድርጎ በመቀየር አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.