የመምህራችን የመምህር ዘላለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የሰድስት ወር መታሰቢያ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 30 ቀን ጠዋት 12:30 ጀምሮ ክቡር ሥጋቸው ባረፈበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎተ ፍትሐት ታስቦ ይውላል።
መምህር ዘላለም በሕይወተ ሥጋ በነበሩበት ወቅት በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ይሰረሀ እንደነበር ይታወቃል።ለአብነት እንዲሆን ከብዙ በጥቂቱ:-
1. ቁጥራቸው ከ300 መቶ በላይ የሚሆኑ አረጋዊያንና አረጋዊያትን መደበኛ በሆነ ሁኔታና በተለየ መርሐ ግብር መመገብ።
2. ከ200 በላይ የሆኑ ሕፃናትን ለአካለ መጠን ደርሰው ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ መንከባከብና በቋሚነት መርዳት።
3. በሰበታ አካባቢ የሚገኙ በቁጥር ከ80 በላይ ዓይነ ስውራንን በማህበር አቅፎ ድጋፍ ማድረግ።
4. በገጠር አካባቢ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን ማነጽ። ከእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አሁን ላይ እንኳን ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የምዕመናንን ድጋፍ የሚፈልጉ ሶስት አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ።
5. በርካታ አደባባይ ላይ ወጥተው መለመን የማይችሉ ወገኖችን ያሉበት ድረስ በመሄድ እያገኙ ድጋፍ ማድረግና ሌሎች በርካታ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በስውር ሲሰሩ የነበሩ ታላቅ መምህር ነበሩ።
በመሆኑም እነዚህን እና ሌሎች መምህር ሲሰሯቸው የነበሩትን የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በአንድ ላይ አቅፎ ለማስቀጠል በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ የሚደረገው “የመምህር ዘላለም ወንድሙ የመታሰቢያ ድርጅት” እየተቋቋመ እንዳለ በዚሁ አጋጣሚ ለመገልጽ እንወዳለን።
የመምህር ዘላለምን አርአያ ፍኖት በመከተል ከሁላችንም የሚጠበቀውን መንፈሳዊ ግዴታ እንወጣ። ለዚህም ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ በጊዜያዊ ኮሚቴ ስም በተከፈተ ንግድ ባንክ ገቢ ማድረግ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000751862192
Source: FastMereja







No comments yet.