በአጥር በመዝለል የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመሰረተበት፡፡

- Advertisement -
Sidebar AD

ቴዲ መኳንንት የተባለው ግለሰብ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ጉርድ ሾላ ሚሽን ትምህርት ቤት አካባቢ ከሚገኝ መኖሪያ ቤት ከሌሊቱ 9፡00 ገደማ ነው።

ተጠርጣሪው በተጠቀሰው መኖሪያ ቤት በአጥር በመዝለልና የመኖሪያ ቤቱን መስኮት አንሸራቶ በመግባት ጠቅላላ ግምቱ 684ሺህ ብር የሚያወጣ ሁለት ታብሌቶች እና የተለያየ ሞዴል ያላቸው 4 ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ሰርቆ ተሰውሯል፡፡

የግል ተበዳይ ጉዳዩን በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ለየረር አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው አመልክተዋል፡፡

ፖሊስ የቀረበለትን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ባከናወነው ክትትል አንድ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተጠርጣሪውን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር በማዋል ክስ ማስመስረቱን የየረር አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ነዋሪዎች ከመተኛታቸው በፊት የመኖሪያ ቤት መስኮት መዘጋቱን በአግባቡ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለወንጀል መፈፀም ምቹ ሁኔታዎችን አስቀድሞ በመከላከል ተፈጽሞ ሲገኝም በአቅራቢያ ላለ የፖሊስ መምሪያ ማሳወቅ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2