የ7 ዓመት ህፃን አግታ 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በጎንደር ከተማ ተያዘች

- Advertisement -
Sidebar AD

በአዲስ አበባ ከምትሰራበት ቤት የ7 ዓመቷን ህፃን አግታ ወደ ጎንደር በመውሰድ ከቤተሰቦቿ 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በጎንደር ከተማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች።

የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዳስታወቀው፣ መቅደስ ሞገስ የተባለችው ተጠርጣሪ ህፃኗን ካገተች በኋላ ወደ ጎንደር በመውሰድ በማራኪ ክፍለ ከተማ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ባለ ጫካ ውስጥ ደብቃት ነበር።

የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ እንደገለጹት፣ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዋን መያዝ ችሏል።

ተጠርጣሪዋ ከግርማ ወንድአሁን ከተባለ የአክስቷ ልጅ ጋር በመተባበር ድርጊቱን እንደፈፀመች ፖሊስ ገልጿል። ሁለቱ ለህፃኗ ቤተሰቦች በስልክ በመደወል 3 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሲሆን፣ ከ370 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ መቀበላቸውም ተገልጿል።

ፖሊስ በጉዳዩ የተሳተፉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም ለመያዝ ክትትል እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

addisreporter2


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2