#Ethiopia | በፈረንጆቹ 1916 አሜሪካ ወደ አንደኛው የዓለም ጦርነት እንድትገባ የሚደረገው ግፊት በርትቶ ሲመጣ ጦርነቱን የሚቃወሙ ወገኖች አንድ ድንቅ ሀሳብ አቅርበው ነበር።
ሃሳቡ ሀገሪቱ ወደ ጦርነት ከመግባቷ በፊት በኮንግረስ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን መላው የአሜሪካ ሕዝብ ድምፅ እንዲሰጥበት የሚጠይቅ ነበር።
ይህም በመላ ሀገሪቱ የጦርነት ህዝበ ውሳኔ ይደረግ የሚል ነበር።
በዚሁ ጊዜ የናብራስካ ግዛት ዜጎች ደግሞ የበለጠ ጥብቅ የሆነ ጥያቄ አቀረቡ።
በሕዝበ ውሳኔው ወቅት አዎ ጦርነት እንውጣ ብሎ የመረጠ ማንኛውም ሰው ወዲያውኑ ስሙን ለውትድርና አገልግሎት በበጎ ፍቃደኝነት ማስመዝገብ አለበት የሚል ነበር።
የዚህ ሀሳብ ዋና አላማ ጦርነትን የሚደግፉ ሰዎች ውጤቱን የሕይወት መስዋዕትነትን እራሳቸው ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን አለባቸው የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነበር።
ሰዎች የራሳቸው ወይም የልጆቻቸው ሕይወት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ሲያውቁ ለጦርነት ድምፅ ከመስጠታቸው በፊት በጥልቀት እንዲያስቡ ማድረግ ሌላው ጉዳይ ነበር።
ምንም እንኳን ይህ ሃሳብ በወቅቱ በሕግ ደረጃ ባይጸድቅም እስከዛሬ ድረስ የሚለው የፍልስፍና እና የፖለቲካ ጥያቄ ሲነሳ በምሳሌነት ይጠቀሳል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#Ethiopia #GetuTemesgen
#America #worldWar #Referendum #History
Source: GetuTemesgen









No comments yet.