እናቷ በተገኙበት ከከባድ ጉዳት ድና ኮከብ የሆነችዋ ተጫዋች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ዙር ውድድር በሀዋሳ ከተማ እየተደረገ ይገኛል።

የ25ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከዕሁድ ጀምሮ እየተካሄዱ ነው። ከእነዚህ መርሃግብሮች መካከል ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከድሬደዋ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ አንዱ ነው።

ጨዋታው በቂርቆስ የ2ለ0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ጎሎቹን በ20 እና 25ኛው ደቂቃ ላይ ምርቃት ፈለቀ አስቆጥራለች።

ጎል አስቆጣሪዋ ምርቃት በጨዋታው 70ኛ ደቂቃ ላይ ከድሬደዋ ተጫዋች ደመቀች ዳልጋ ጋር ተጋጭታ ጉዳት አጋጥሟታል።

ጉዳቱ በባለሙያዎቹ አገላለፅ ”ምላስ ከተለመደው ቦታ ስቶ ከስር ያሉት ጡንቻዎች ህመም ሲያጋጥማቸው እና በነፃነት አየር ለመተላለፍ ሲቸገር” የሚገጥም እንደሆነ ተገልጿል።

ተጫዋቿ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ራሷን ስታ ወድቃ ህክምና ሲደረግላት እናቷ በስቴዲየም ተገኝተው ጨዋታውን እየተመለከቱ ነበር።

ከኤፍ ኤም አዲስ 97. 1 ጋር ቆይታ ያደረገችው ምርቃት ስለሁኔታው አስረድታለች።

“እናቴ ሁሌም ታበረታታኛለች ጨዋታዎችን ታያለች። በሁኔታው በጣም ተደናግጣ ነበር። ለእናት ከባድ ነው ጉዳቱ ከባድ ነበር። አሁን ግን በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ” ብላለች::

ምርቃት ፈለቀ በዕለቱ የማሸነፊያ ጎሎች ከማስቆጠሯም ባለፈ ከአወዳዳሪው አካል የሚዘጋጀውን የጨዋታ ኮከብ ሽልማትን ወስዳለች።

ኑራ ኢማም

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1