የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተጠናቀው የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ታውቀዋል። መድፈኞቹ እና የባቫሪያው ግዙፍ ሙኒክ ድል ቀንቷቸዋል።
አርሰናል ወደ ግማሽ ፍፃሜ!
ውጤት፦ አርሰናል 0 – 0 ስፖርቲንግ ሊዝበን (ድምር ውጤት፦ 1 – 0)
በመጀመሪያው ዙር ከሜዳው ውጪ ያስመዘገበው የ 1 ለ 0 ድል አርሰናልን ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ወደ ግማሽ ፍፃሜ አሳልፎታል። አርሰናል ለፍፃሜ ለመድረስ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ብርቱ ፍልሚያ ያደርጋል።
ባየር ሙኒክ ሪያል ማድሪድን አስወጣ!
ውጤት፦ ባየር ሙኒክ 4 – 3 ሪያል ማድሪድ (ድምር ውጤት፦ 6 – 4)
በአሊያንዝ አሬና በተደረገው አስገራሚ ጨዋታ ሃሪ ኬን፣ ፓቭሎቪች፣ ሉዊስ ዲያዝ እና ሚሼል ኦሊሴ የሙኒክን ግቦች አስቆጥረዋል።
ሪያል ማድሪድ በአርዳ ጉለር እና ምባፔ ግቦች ቢታገሉም፣ የካማቪንጋ በቀይ ካርድ መውጣት ዋጋ አስከፍሏቸዋል። ሙኒክ በግማሽ ፍፃሜው ከፒኤስጂ ጋር ይገናኛል።
የግማሽ ፍፃሜ ድልድል፦
አርሰናል 🆚 አትሌቲኮ ማድሪድ
ባየር ሙኒክ 🆚 ፒኤስጂ
#getu #ChampionsLeague #UCL #Arsenal #BayernMunich #RealMadrid #HarryKane #Mbappe #FootballNews #SemiFinals #ሰበርዜና #አርሰናል #ባየርሙኒክ #ሻምፒዮንስሊግ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen
Source: GetuTemesgen









No comments yet.