የእስራኤልና የሊባኖስ መሪዎች በመካከላቸው የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በደስታ ተቀብለውታል።
ኔታንያሁም “ታሪካዊ የሰላም ስምምነት ለማድረግ እድል” እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለአስር ቀናት የሚቆይ ሲሆን የሚደረጉ ድርድሮች የለውጥ ምልክቶችን ካሳዩ “በጋራ ስምምነት” ሊራዘም ይችላል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ዝርዝር መረጃ መሰረት ስምምነቱ የሚከተሉትን ነጥቦች ይዟል።
👉 እስራኤል “በማንኛውም ጊዜ፣ በታቀዱ፣ በተጨባጭ ወይም በቀጣይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች ራሷን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ የመውሰድ” መብት ይኖራታል።
👉ሊባኖስ፣ ሄዝቦላህ እና ሌሎች “ከመንግሥት ውጭ የሆኑ የታጠቁ ቡድኖች” በእስራኤል ዒላማዎች ላይ ጥቃት እንዳይሰነዝሩ ለመከላከል “ትርጉም ያላቸውን እርምጃዎች” መውሰድ አለባት።
👉በስምምነቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት የሊባኖስ የጸጥታ ኃይሎች ለሊባኖስ ደህንነት ብቸኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይገነዘባሉ።
👉እስራኤል እና ሊባኖስ “ቀሪ ጉዳዮችን ሁሉ ለመፍታት” አሜሪካ ተጨማሪ ቀጥተኛ ውይይቶችን እንድታመቻች ጠይቀዋል።
መግለጫው አክሎም የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስራኤል በሁለቱ ወገኖች መካከል “በቀና ልቦና ዘላቂ የጸጥታ እና የሰላም ስምምነት ለመድረስ የሚደረግ ድርድር” ለማስቻል “መልካም ፈቃደኝነቷን” ያሳየችበት እንደሆነ ገልጿል።
ሄዝቦላህ በተኩስ አቁም ስምምነቱ ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆኑን ያሳየ ቢሆንም፣ በሊባኖስ ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን “ሙሉ በሙሉ እንዲቆሙ” እና “የእስራኤል ኃይሎች የመንቀሳቀስ ነፃነት እንደሌላቸው” የሚሉ ሃሳቦች መካተት እንዳለበት ተናግሯል።









No comments yet.