የአምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ይፈጸማል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የቀድሞዋ አንጋፋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ቅዳሜ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈጸም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በመርሐ-ግብሩ መሰረት የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ከቀኑ 8 ሰዓት በእንጦጦ ኪዳነ-ምህረት ቤተክርስቲያን የሚፈጸም ይሆናል።

አምባሳደር ቆንጂት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን በ1950ዎቹ በለጋ እድሜያቸው ተቀላቅለው ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት አገልግለዋል።

አምባሳደር ቆንጂት ከዮዲት እምሩ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደርም ናቸው።

አምባሳደሯ በኦቶዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭና ቬይና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በአፍሪካ ህብረትና በተባባሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንም ቋሚ መልዕክተኛ በመሆን ሰርተዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#EthiopianBroadcastingCorporation #Ethiopia #Diplomacy #AmbassadorKonjitSineGiorg


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: