የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ረድኤቱ እና ምልጃው አይለየን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ።

ከፍጥረታት አስቀድሞ አምላኩን ዐውቆ ስብከት የጀመረ፣ የዲብሎስን ሐሰተኛነት ያጋለጸ መልአክ ነው፤ ስለዚህም ነገረ ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበሥር በመመረጡ አብሳሬ ትስብእት፣ መልአከ ብሥራት፣ መጋቤ ሐዲስ ይባላል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ሁልጊዜም ለደስታና ለምሥራች የሚላክ መልአክ ይለዋል፡፡ ከዚህ በኋላም ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ ዘወትር በምንጸልያቸው አቡነ ዘበሰማያት፣ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል፣ ውዳሴ ማርያም፣ ይዌድስዋ መላእክትን በመሳሰሉት ጸሎቶች ዘወትር ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡ ካህናት አባቶች ስእለት ሰሚ፣ ፈጥኖ ደራሽ መልአክ ይሉታል፤ በክርስቲያኖችም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ መልአክ ነው፡፡

ስለዚህም ፈጥኖ ደራሹ መልአክ፣ ስእለት ሰሚው መልአክ ይባላል፡፡ በኅዳር ወር ድርሳነ ገብርኤል ምዕራፍ 2፥13 “ወንድሞቻችን ሆይ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከመላእክት ሁሉ ይልቅ ቅዱስ ገብርኤልን በይበልጥ እንደምትወደው ተመልከቱ፤ የልጅዋን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ መወለድ ያበሠራት እርሱ ነውና” ተብሎ እንደተጻፈው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ከሌሎች መላእክት ሁሉ አስበልጣ ትወደዋለች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በራእይ 18፥1 “ከዚህ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች፡፡” ይገልጸዋል፡፡

ደግሞም በራእይ 10፥1 “ብርቱ መልአክ ደመና ተጎናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤ የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ፤ ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሳም አንበሳ በታላቅ ድምጽ ጮኸ” በማለት የቅዱስ ገብርኤልን ኃያልነት መስክሯል፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ዓለምንና ክብሯን ንቀው ለነፍሳቸው ካደሩ ገዳማውያን ዘወትር አይለያቸውም፡፡ በጸሎታቸው በጠሩት ጊዜም ሊራዳቸው ፈጥኖ ይደርሳል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2