የታላላቆቹ ፍልሚያ በስታምፎርድ ብሪጅ!
#Ethiopia | ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ በመላው ዓለም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች አይን ወደ ለንደን፣ ስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ያርፋል። ቼልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድ ለክብር እና ለአራቱ ውስጥ የመቀመጥ ተስፋቸው ወሳኝ የሆነውን ፍልሚያ ያደርጋሉ።
የሁለቱ ቡድኖች ወቅታዊ ሁኔታ፦
ቼልሲ (ሊያም ሮሲኒየር)፦
በሊጉ 6ኛ ደረጃ ላይ ቢገኝም፣ ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች በደረሰበት ሽንፈት ጫና ውስጥ ነው። የዛሬው ሽንፈት ታሪካዊውን የሽንፈት ሰንሰለት እንዳይደግም ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ (ማይክል ካሪክ)፦
በ55 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ባለፈው ሳምንት ከሊድስ የደረሰበትን አስደንጋጭ ሽንፈት ለመርሳትና ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ለማረጋገጥ ሦስት ነጥብ የግድ ያስፈልገዋል።
የታሪክ ማህደር (Head-to-Head)፦
ጠቅላላ ግንኙነት፦
198 ጊዜ ተገናኝተው ዩናይትድ 81 ጊዜ ሲያሸንፍ፣ ቼልሲ 56 ጊዜ ድል ቀንቶታል። 61 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
የሜዳ ላይ የበላይነት፦
ዩናይትድ በስታምፎርድ ብሪጅ ካደረጋቸው ያለፉት 12 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ መሆኑ ለቼልሲ የሞራል የበላይነት ይሰጣል።
ደርሶ መልስ፦
ዩናይትድ ዛሬ ካሸነፈ፣ ከ2019/20 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቼልሲን በደርሶ መልስ (Home & Away) ያሸነፈበት ዓመት ይሆናል።
የማይሰለፉ ተጫዋቾች፦
ቼልሲ፦
ሪስ ጄምስ፣ ሌቪ ኮልዊል እና ትሬቮ ቻሎባ (በጉዳት)
ማንችስተር ዩናይትድ፦
ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ሃሪ ማጓየር (በቅጣት)፣ ሌኒ ዮሮ (በጉዳት)
”በለንደን ሰማይ ስር ማን ይነግሳል?
ሰማያዊዎቹ ወይስ ቀያይ ሰይጣኖቹ?”
ግምታችሁን አጋሩኝ!
#getu #PremierLeague #CHEmun #Chelsea #MUFC #StamfordBridge #MichaelCarrick #LiamRosenior #FootballEthiopia #EPLUpdate #ቼልሲ #ማንችስተርዩናይትድ #ፕሪሚየርሊግ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen
Source: GetuTemesgen









No comments yet.