በኢራን ጦርነት ምክንያት የኮንዶም ዋጋ በ30% ሊንር ነው! በዓለማችን ግዙፉ የኮንዶም አምራች ኩባንያ ካሬክስ በኢራንና በአሜ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በኢራን ጦርነት ምክንያት የኮንዶም
ዋጋ በ30% ሊንር ነው!

በዓለማችን ግዙፉ የኮንዶም አምራች ኩባንያ ካሬክስ በኢራንና በአሜሪካ/እስራኤል መካከል ባለው ጦርነት ምክንያት የዋጋ ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ። በማሌዥያ የሚገኘውና በዓመት ከ5 ቢሊዮን በላይ ኮንዶሞችን የሚያመርተው ይህ ኩባንያ፣ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ መዘጋት ምክንያት የጥሬ ዕቃዎችና የነዳጅ አቅርቦት በመስተጓጎሉ የምርት ወጪው በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮበታል። በዚህም ምክንያት የኮንዶም ዋጋ እስከ 30 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ ሊጨምር እንደሚችል የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጎህ ሚያህ ኪያት አስጠንቅቀዋል።
የኩባንያው ኃላፊ እንደገለጹት፣ በጦርነትና በኢኮኖሚ አለመረጋጋት ወቅት ሰዎች ተጨማሪ የቤተሰብ ወጪን ለመቀነስ ሲሉ የኮንዶም ፍላጎት በ30 በመቶ ገደማ ይጨምራል። ይሁን እንጂ የጭነት መርከቦች ጉዞ መስተጓጎል የሲሊኮንና አሞኒያ ግብዓቶችን ለማግኘት አስቸጋሪ አድርጎታል። ይህ የዋጋ ጭማሪ በኮንዶም ላይ ብቻ ሳይሆን በአውሮፕላን ትኬት፣ በማዳበሪያ፣ በምግብና በኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ላይም ተፅዕኖ እያሳደረ ሲሆን፣ የዓለም የንግድ መስመር መዘጋት የሸማቾችን ኑሮ ከባድ እያደረገው ይገኛል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: